ተጨዋች ያለፈቃድ በመሳም የተከሰሰው የቀድሞው የስፔን እግርኳስ ኃላፊ ቅጣት ተላለፈበት
ሩቢያልስ በሽልማት ስነስርአቱ ላይ ተጨዋቿን የሳመው ፈቅዷ እንደሆነ ሲከራከር የቆየ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የሄርሞሶ ምስክርነት ፈቃደኛ አለመሆኗን የሚያሳይ ነው ብሏል

የስፔን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሩቢያልስ ሄርመሶ የተባለችውን ተጨዋች ያለፈቃዷ በመሳም ጾታዊ ጥቃት ማድረሱን አረጋግጦ 10ሺ ዩሮ እንዲከፍል ወስኖበታል
ተጨዋች ሳያስፈቅድ በመሳም ተከሶ የነበረው የቀድሞው የስፔን እግርኳስ ኃላፊ ቅጣት ተላለፈበት።
በሀገሪቱ አነጋጋሪ የነበረውን ጉዳይ ሲያይ የቆየው የስፔን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞው የእግር ኳስ ፌደሬሽን ኃላፊ ሊዩስ ሩቢያልስ ጀኒ ሄርመሶ የተባለችውን ተጨዋች ያለፈቃዷ በመሳም ጾታዊ ጥቃት ማድረሱን አረጋግጦ 10ሺ ዩሮ እንዲከፍል ወስኖበታል።
ሮይተርስ አየሁት ባለው የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሩቢያልስ አስገደዶ ስሟል በሚል የቀረበበት ክስ ውድቅ ተደርጎለታል።
"መዋጋቴን እቀጥላለሁ" ሲል ሩቢያልስ አቤቱታ እንደሚያቀርቡ ለሮይተርስ ተናግሯል።
የተጨዋቿ ሄርሞስን ጠበቃ አንጀል ቻቫሪያ ተጨማሪ ዝርዝር ባይሰጡም አቤቱታ እንደሚያቀርብ መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል።
አቃቤ ህጎች በስፔን ምድር በሴቶች እግርኳስና በመላው የስፔን ማህበረሰብ ውስጥ ስላለው ጾታዊ ጥቃት ጉዳይ ከባድ ክርክር ያስነሳው የ47ቱ ሩቢያልስ በእስር እንዳቀጣ ፈልገው ነበር።
ሄርሞሶን በ2023 የአለም ዋንጫ የሽልማት ስነ ስርአት ላይ የተሳመችው በፈቃዷ እንደሆነ እንድትናገር ለማስገደድ ሞክረዋል የተባሉ ከሩበያልስ ጋር የተከሰሱ ሶስት ተከሳችን ፍርድ ቤቱ በነጻ አሰናብቷቸዋል።
ሩቢያልስ በሽልማት ስነስርአቱ ላይ ተጨዋቿን የሳመው ፈቅዷ እንደሆነ ሲከራከር የቆየ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የሄርሞሶ ምስክርነት ፈቃደኛ አለመሆኗን የሚያሳይ ነው ብሏል።
የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ዳኛ ፈርናንድዝ ፔሪዮቶ ሩቢያልስን ጾታዊ ጥቃት በማድረስ ጥፋተኛ ሆኖ አግኝተውታል። ነገርግን ዳኛው እንዳሉት ድርጊቱ ማስፈራሪያ ወይም ጥቃት የሌለበት በመሆኑ በክብደቱ አነስተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ዳኛው ሩቢያልስ ከመሳም ያለፈ ከባድ ድርጊት ባለመፈጸሙ ምክንያት ከእስር ቅጣት ሊተርፍ ችሏል ብለዋል።
ሩቢያልስ ተጨዋቿ ሄርሞሶ ካለችበት 200 ሜትር ሪዲየስ ርቆ እንዲንቀሳቀስና ለአንድ አመት ያህል ከእሷ ጋር ከመነጋገር እንዲቆጠብ ውሳኔ ተላልፎበታል።
ሩቢያልስ በ18 ወራት ውስጥ ለሄርሞሶ 3000 ዩሮ በካሳ መልክ እንዲከጣት ተወስኖበታል። በፌደሬሽኑ የሩቢያልስ አመታዊ ደሞዝ 675,762 ዩሮ ነበር።
ሄርሞሶ በፍርድ ቤት በቀረበችበት ወቅት ያለፈቃዷ የተፈጸመባት የመሳም ድርጊት "በህይወቴ ደስተኛ የሆንኩበትን ቀን አበላሽቷል" ያለች ሲሆን የቡድን ጓደኞቿም በቀጣይ ሰአታትና ቀናት ደክሟትና ስታለቅስ እንደነበር መስክረዋል።