የስፔን ስፖርት ፍርድቤት ተጨዋች በመሳም ውዝግብ ባስነሳው ኃላፊ ላይ ምርመራ ከፈተ
ሩቢያልስ ለፈጸመው ድርጊት ይቅርታ ቢጠይቅም ይህ በቂ አይደለም ስልጣን ልቀቅ የሚል ግፊት በርትቶበታል
ሩቢያልስ ስልጣንን እንደማይለቅ እና መሳሳሙም በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው የሚል መከራከሪያ እያቀረበ ነው
የስፔን የስፖርት ፍርድ ቤት በአለም ዋንጫ ጨዋታ የድል አከባበር ወቅት ተጨዋች በመሳም ውዝግብ ባስነሳው የስፔን እግር ኳስ ኃላፊ ሩቢያልስ ላይ ምርመራ ከፍቷል።
የስፔን ስፖርት አድሚኒስትሬቲቭ ትሪቡናል(ቲኤዲ) የስፔን ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በአለም ዋንጫ ጨዋታ የፍጻሜ ውድድር እንግሊዝን 1-0 ካሸነፈ በኋላ በነበረው የድል አከባበር ላይ ሩቢያልስ አሳይቷል ባለው ተገቢ ያልሆነ ባህሪይ ላይ ምርመራ ጀምራል።
ሩቢያል ድል ላደረጉት ተጨዋቾች ሜዳሊያ በሚያጠልቅበት ወቅት ሄርሞሶ የተባለችውን ተጨዋች ያለፈቃዷ በመሳሙ ውግዘትና ቁጣ ማስተናገዱ ይታወሳል።
ሩቢያልስ ለፈጸመው ድርጊት ይቅርታ ቢጠይቅም ይህ በቂ አይደለም ስልጣን ልቀቅ የሚል ግፊት በርትቶበታል።
አለምአቀፉ የስፖርት አካል(ፊፋ) ምርመራውን እስከሚጨርስ ድረስ ከሁሉም አይነት የስፖርት እንቅስቃሴዎች ማገዱን መግለጹ ይታወሳል።
ተጨዋቿ ሄርሞሶንም እንዲህ አይነቱ ተግባር በዝምታ ሊታለፍ አይገባም የሚል አስተያየት ሰጥታለች።
ሩቢያልስ ስልጣንን እንደማይለቅ እና መሳሳሙም በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው የሚል መከራከሪያ እያቀረበ ነው። ነገርግን ሄርሞሶ ለመሳም ፍቃደኛ አልነበርኩም ብላለች።