ኮሮና “ባጠፋነው ጥፋት ምክንያት“ ትልቅ ቅጣት ከመምጣቱ በፊት የመጣ ማንቂያ ነው-ኡስታዝ አቡበከር
ረመዳን በቤት ማሳለፍ “ታሪካዊ አጋጣሚ ነው፤ ሳንጠቀምበት እንዳናልፋ”-ኡስታዝ አቡበከር
መስጅዶች መዘጋታቸው “ከነበረን ልምድ ወጥተን በአዲስ መልክ ከአላህ ጋር የበለጠ የምንገናኝበት” እድል ይሰጣል- ኡስታዝ አቡበከር አህመድ
መስጅዶች መዘጋታቸው “ከነበረን ልምድ ወጥተን በአዲስ መልክ ከአላህ ጋር የበለጠ የምንገናኝበት” እድል ይሰጣል- ኡስታዝ አቡበከር አህመድ
ኡስታዝ አቡበከር አህመድ የዘንድሮ ረመዳን ጾም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት መስጅዶቸ በተዘጉበት ወቅት መሆኑ እንደ ትልቅ ታሪካዊ አጋጣሚ በመውሰድ ህዝበ ሙስሊሙ ሊጠቀምበት ይገባል ብለዋል፡፡
ከአል-አይን አማርኛ ጋር ቆይታ ያደረጉት ኡስታዝ አቡበከር የረመዳን ጾም በጥሞና የምናሳልፍበት ጊዜ በመሆኑ በቤት ውስጥ ማሳለፉ “ከነበረን ልምድ ወጥተን በአዲስ መልክ ከአላህ ጋር የበለጠ የምንገናኝበት” መሆኑን ተናግረዋል፡፡
“ ‘ብዙዎቹ አስሉ[ትክክለኛ ቦታው] ቤት ነው ይላሉ’፤ ቤት ላይ ደግሞ የጥንካሬ መገለጫ ነው” ብለዋል ኡስታዝ አቡበከር፡፡
“ብዙ ጊዜ መስጅድ መስጥተን የምንላቸውን ሱናዎች ቤታችን ገብተን እንረሳቸዋለን፤ አሁን ላይ በትክክል ለአላህ ባርነታችንን የምናሳይበት፤ ለሱ የምንዋደቅበትና ለሱ ታዛዥነታችንን የምንገልጽበት ነው” ያሉት እስታዝ አቡበከር ጾሙን በቤት መሳፍ ቁርአንን ብዙ ጊዜ ለማንበብ እድል እንደሚሰጥም ገልጸዋል፡፡
ኡስታዝ አቡበከር እንደገለጹት በቤት ውስጥ በመሆን “በወር እንድ ጊዜ ቁርአንን ያነብ የነበረ ሰው፣ ሁለትና ሶስት ጊዜ፣ በወር 10 ጊዜ ያነብ የነበረ ሰው 15-20 ጊዜ“ አንዲያነብ እድል ይፈጥራል፡፡
“የረመዳን ባህርይ ብዙ ጊዜ የማንረዳው ከልምድ የምናጠናክራቸው ነገሮች አሉ፤ አብሮ ማፍጠሩ ይወደዳል፤ አብሮ መስገዱ ይወደዳል፤ ረመዳን አንዱና ትልቁ የሚወደደው ሌላው ባህሪው ምልባትም እኛ የዘነጋነው አንደማህበረሰብ አጣነው ብየ የማስበው ኡዝላውን[መገለል]ፓርት ነው፤ ለአላህ እራስን መስጠቱን ነው፡፡”
ኡስታዝ አቡበከር ይህን እድል በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መላው አለምን ስጋት ውስጥ ውስጥ ከቷል፤ ስለሆነም ይህ ጊዜ እርቅና ወደ አላህ መመለስን እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡
ስለ ወረርሽኑ “እንደ ሙስሊም ማህበረሰብ እንደ አማኝ የምናስበው ነገር አለ” ያሉት ኡስታዝ ቡበከር አንደኛው ፈታና ነው፤ ሁለተኛ ደግሞ ባጠፋነው ጥፋት ምክንያት ትልቅ ቅጣት ከመምጣቱ በፊት የመጣ ማንቂያ ነው ብለዋል፡፡
ኡስታዝ አቡበከር በሆኑም ይህ ወቅት የበለጠ ወደ አላህ የመንሸሸግበት ጊዜ ነው ብለዋል፡፡
ረመዳን “ከጭንቀት ጫና፣ ከማህረሰብ ቅልቅል ውጥተህ ከአላህ ጋር ብቻ የምታደረገው ግኙነት” መሆኑን የገለጹት ኡስታዝ አቡበከር “ይሄ ፍርሳ[ እድል] ነው” ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ፕሬዘዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ኢድሪስ ህዝብ ሙስሊሙ በዚህ ሳምንት የሚጀመረውን የረመዳን ጾም በተለያዩ የአምልኮ ተግባራት በማከናውን በቤቱ እንዲያከብር ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
በኢትዮጵያ እስካሁን ሶስት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሲሆን በቫይረሱ የተጠቁት ቁጥር ደግሞ 117 ደርሷል፡፡