ከኮሮና ቫይረስ ጉዳት ማገገም ያልቻለው አየር መንገዱ የ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ አጋጥሞኛል ብሏል
የአሜሪካው ስፕሪት አየር መንገድ ኪሳራ ውስጥ መግባቱን አመነ፡፡
ዋና መቀመጫውን ፍሎሪዳ ያደረገው ስፕሪት አየር መንገድ ኪሳራ ላይ መሆኑን በይፋ የገለጸ ሲሆን ከመፍረስ የሚታደገውን እርምጃ በመውሰድ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ በተለይም ከኮሮና ቫይረስ መከሰት በኋላ ማገገም እንዳልቻለ ገልጾ የ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ደርሶብኛል ብሏል፡፡
ኪሳራውን ተከትሎም የአየር መንገዱ አንድ አክስዮን ዋጋ የ25 በመቶ ቅናሽ እንዳሳየ ቪኦኤ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ አየር መንገዱ በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ተጨማሪ አንድ ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ይጠብቀዋል፡፡
አየር መንገዱ በተለይም ኪሳራውን ለመከላከል ከሌላኛው የአቪዬሽን ተቋም ጀት ብሉ ጋር ለመዋሀድ በድርድር ላይ የነበሩ ቢሆንም ድርድሩ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
የአየር መንገዱ ስራ አስፈጻሚ ቴድ ክርስቲ በበኩላቸው ድርጅቱን ከከፋ ኪሳራ ለማዳን የመድህን ጥያቄ ለባለ አክስዮኖች እና መንግስት ጥያቄ እንዳቀረቡ ተናግረዋል፡፡
በቢሾፍቱ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የኤሌክትሪክ ችግር እንዳለበት አስቀድሞ ይታወቅ ነበር ተባለ
ስራ አስፈጻሚው አክለውም መንገደኞች አሁንም ቲኬት መቁረጥ እና የበረራ አገልግሎቶችን ማግኘት እንሚችሉ በዋጋ ላይም የሚደረግ ለውጥ እንደማይኖር አክለዋል፡፡
የኮሮና ቫይረስ በተለይም የአቪዬሽን ተቋማትን ክፉኛ ጎድቶ ያለፈ ሲሆን የቫይረሱ ስርጭት ሲቀንስ ብዙዎች ወደ ቀድሞ አቋማቸው ቢመለሱም ስፕሪት አየር መንገድ ግን እስካሁን ኪሳራ ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡
በአሜሪካ አቪዬሽን ታሪክ ስፕሪት አየር መንገድ ለኪሳራ የተዳረገ ብቸኛው አየር መንገድ አይደለም የተባለ ሲሆን ሀገሪቱ ተቋሞቿን ከኪሳራ እና መፍረስ መታደግ የሚያስችል አንቀጽ 11 የተሰኘ የድጋፍ ህግ አላት፡፡