የኮሊስትሮል መድሃኒትን የሰሩት ተመራማሪ ህይወታቸው አልፈ
ፔንስሊን ለተሰኘው መድሃኒት መገኘት መነሻ የሆኑት ጃፓነዊ ተመራማሪ በ90 ዓመታቸው ህይወታቸው አለፈ
ተመራማሪው በህክምና ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የኖቤል ሽልማት አለመሸለማቸው ብዙዎችን አስቆጭቷል
የኮሊስትሮል መድሃኒትን የሰሩት ተመራማሪ ህይወታቸው አልፈ፡፡
አኪራ ኤንዶ በ1933 በገጠራማው የጃፓን አካባቢ ተወልደው በመላው ዓለም ያሉ ህመምተኞች ፈውስ እንዲያገኙ ያደረጉ ተመራማሪ ነበሩ፡፡
ኤንዱ በተወለዱ በ90 ዓመታቸው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ተመራማሪው በተለይም ከልብ ህመም ጋር ለተያያዙ ህመሞች የሚውለው ስታቲን የተሰኘውን መድሃኒት በማግኘት ይታወቃሉ፡፡
መድሃኒቱ በኮሊስትሮል መብዛት ምክንያት የደም ቧንቧ መጥበብ እና የልብ ምት አለመስተካከል ጋር በተያያዘ በሐኪሞች የሚታዘዝ መድሃኒት ነው፡፡
ጃፓን የሚያገቡ ዜጎቿን ለማበረታታት የመጠባበሻ መተግበሪያ ሰራች
ኤንዱ ለኮሊስትሮል መብዛት እና ተያያዥ ህመሞች ያደረጉት ምርመር ፔንሲሊን ተብሎ ለሚጠራው የጸረ ተዋህሲያን መድሃኒት እንዲሰራ መነሻ ምርምሮችን አድርገዋል ተብሏል፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ተመራማሪው በህክምናው ዘርፍ በርካታ አስተዋጽኦዎችን የበረከቱ ቢሆንም የኖቤል ሽልማት ሳይሸለሙ ህይወታቸው ማለፉ በርካቶችን አሳዝኗል፡፡
ፕሮፌሰር ኢንዱ በፈረንጆቹ 1963 ላይ ያገኙት መድሃኒት በደም ውስጥ ያለውን የስብ መጠን እንዲቀንስ የሚያደርግ ሲሆን ደም በሰውነታችን ውስጥ በሚገባ እንዲዘዋወር የሚያደርግ ነው፡፡