በደቡባዊ ጃፓን የተከሰከሰው ይህ አውሮፕላን የአደጋ ጊዜ ቅኝት በማድረግ ላይ እንደነበር ተገልጿል
የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን በጃፓን መከስከሱ ተገለጸ፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል የሆነችው አሜሪካ በተለያዩ ሀገራት የጦር ሰፈር ያላት ሲሆን ከነዚህ መካከልም ጃፓን አንዷናት፡፡
በደቡባዊ ጃፓን ባህር ላይ ቅኝት ሲያደርግ የነበረ የጦር አውሮፕላን እንደተከሰከሰ ኤአፍፒ ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ይህ አውሪፕላን ስምንት ሰዎችን አሳፍሮ ነበር የተባለ ሲሆን በአውሮፕላኑ ላይ የነበሩ ሰዎች ደህንነትን የተመለከቱ መረጃዎች እስካሁን ይፋ አልተደረገም፡፡
ፔንታጎን በጃፓን ሰለተፈጠረው ክስተት እስካሁን የተጎጂዎችን ማንነት፣ የአደጋው መንስኤ እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን ይፋ ከማድረግ መቆጠቡም ተገልጿል፡፡
የእስራኤላዊው ቢሊየነር መርከብ በኢራን በድሮን ተመታለች - አሜሪካ
ባሳለፈነው ነሀሴ ወር ላይ በአውስትራሊያ በልምምድ ላይ የነበረ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ በውስጡ የነበሩ ሁሉም ወታደሮች ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡
እንዲሁም ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ኤፍ 16 የተሰኘው የውጊያ አውሮፕላን በደቡብ ኮሪያ ኦሳን አውሮፕላን ማዘዣ አቅራቢያ ተከስክሷል መባሉ አይዘነጋም።
የአውሮፕላኑ አብራሪን ከከፋ ጉዳት መታደግ የተቻለ ሲሆን በአደጋው ሌሎች ንጹሀን ሰዎች ላይ ያደረሰው ጉዳት እንደሌለ ሲኤን ኤን በወቅቱ ዘግቧል።
አውሮፕላኑ ከሰሜን ኮሪያ ሊሰነዘር የሚችልን ጥቃት በኮሪያ ባህረ ሰላጤ ቅኝት በማድረግ ላይ እያለ እንደተከሰከሰ ተገልጿል።