እስራኤልና ኤምሬትስ ስምምነት ከተፈራረመ በኋላ የአሜሪካ ገንዘብ ሚኒስትር መካከለኛ ምስራቅን ሊጎበኙ ነው
እስራኤልና ኤምሬትስ ስምምነት ከተፈራረመ በኋላ የአሜሪካ ገንዘብ ሚኒስትር መካከለኛ ምስራቅን ሊጎበኙ ነው
የአሜሪካው ገንዘብ ሚኒስትር ስቴቨን መኑቺን ወደ እስራኤል፣ ባህሬንና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚሄደረውን የአሜረካ ልኡክ እንደሚመሩ የአሜሪካ ገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ጉብኝቱየተባበሩት አረብ ኤምሬትና ባህሬን ከእስራኤል ጋር መደበኛ ግንኙነት ለመመስረት መስማማታቸውን ተከትሎ ነው፤ ባህሬንና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሩብ ክፍለዘመን ውስጥ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት በመመስረት የመጀመሪያዎቹ የአረብ ሀገራት ሆነዋል፡፡
የባህሬንና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት መጀመር በፈሊስጤም ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም፡፡
የእስራኤልና የተባባሩት አረብ ኤምሬትስን ግንኙነት እንዲመሰርቱ ስትሰራ የነበረው አሜሪካ ነበረች፡፡
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስምምነቱን ታሪካዊና ለመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ያሰፍናል ሲሉ ማድነቃቸው ይታወሳል፡፡