ትራምፕ የወሲብ ፊልም ተዋናይ ከሆነችው ዳንኤልስ ጋር የፈጸሙት ግንኙነት ለህዝብ ጆሮ እንዳይደርስ ገንዘብ በድብቅ ከፍለዋል በሚል ተጠርጥረዋል
ትራምፕ የወሲብ ፊልም ተዋናይ ከሆነችው ዳንኤልስ ጋር የፈጸሙት ግንኙነት ለህዝብ ጆሮ እንዳይደርስ ገንዘብ በድብቅ ከፍለዋል በሚል ተጠርጥረዋል
ስቶርሚ ዳንኤል ዶናልድ ትራምፕ ወደ ወህኒ ቤት እንዲወርዱ አልፈልግም አለች፡፡
45ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ በገንዘብ ማጭበርበር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ክስ የተመሰረተባቸው በፈረንጆቹ 2006 የወሲብ ፊልም ተዋናይ ከሆነችው ስቶርሚ ዳንኤልስ ጋር ወሲብ ፈጽመዋል የሚል ዘገባ በ2018 ወጥቶባቸዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ከስቶርሚ ዳንኤልስ ጋር ፈጽመውታል የተባለው ድርጊት ከህዝብ ጆሮ እንዳይደርስ 130 ሺህ ዶላር በጠበቃቸው በኩል ክፍያ መፈጸማቸውን በዚሁ ዘገባ ላይ ተጠቅሶ ነበር፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ጉዳዩን የካዱ ቢሆንም የኒዮርክ አቃቢ ህግ ግን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ለስቶርሚ ዳንኤልስ የከፈሉት የማባበያ ክፍያ በህጋዊ ወጪ አስመስለው የገንዘብ ማጭበርበር ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ክስ መስርቶባቸዋል፡፡
ለዶናልድ ትራምፕ ክስ መመስረት መነሻ የሆነችው ስቶርሚ ዳንኤልስ የቀደሞ ደንበኛዋ እስር ቤት አይገባቸውም ሲሉ ተናግረዋል ተብሏል፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ዶናልድ ትራምፕ በተለይም ከወሲብ ፊልም ተዋናይ ከሆነችው ዳንኤልስ ጋር በፈጸሙት ድርጊት እስር ቤት ሊገቡ አይገባም ብላለች፡፡
ይሁንና ዶናልድ ትራምፕ በተጠረጠሩባቸው ሌሎች ወንጀሎች ጥፋተኛ ከተባሉ ግን ለሌሎች አርዓያ ሊሆኑ ይችላሉ ማለታቸው ተገልጿል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ በያዝነው ሳምንት ማንሃተን ፍርድ ቤት ሲቀርቡ በቴሌቪዥን መመለክቷን የጠናገረችው ዳንኤልስ የተቀላቀሉ ስሜቶችን እንዳስተናገደች ተናግራለች፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ከእንግዲህ አይነኬነታቸው አብቅቶለታል ያለችው ዳንኤልስ እስር ግን አይገባቸውም ማለቷ ተሰምቷል፡፡