ከብዙ አስቸጋሪ የጦር ግንባር ህይወታቸው በተዓምር የተረፉት እኝህ ወታደር በ92 ዓመታችው ህይወታቸው አልፏል
ለአራት ሀገራት የተዋጉት ታሪካዊ ወታደር።
ያንግ ኪዩንግጆንግ ይባላል። ኮሪያዊ ዜጋ ሲሆን በ20ኛው ክፍለዘመን ሀገሩ በጃፓን በተወረረችበት ወቅት ነበር ሳይወድ በግዱ ሀገሩን ነጻ ለማውጣት ወደ ውትድርናው ዓለም የገባው።
ሀገሩን ነጻ ለማውጣት ከጃፓን ጋር እየተዋጋ እያለም ተማርኮ ወደ ግዞት ይወርዳል።
በጃፓን እስር ቤት እያለም ያሰረችው ሀገር ጃፓን ከሶቪየት ህብረት ጋር ወደ ጦርነት ማምራቷን ተከትሎ ግለሰቡ ጃፓንን ወግኖ ሶቪየት ህብረትን እንዲወጋ ወደ ጦር ግንባር እንዲያመራም ተደርጓል።
ይህ ኮሪያዊም ለጃፓን እየተዋጋ እያለ በሶቪየት ጦር በድጋሚ ይማረካል። ለሁለተኛ ጊዜ በጠላት ጦር የተማረከው ያንግ ለአመታት በእስር ቤት ለማሳለፍ ተገዷል።
ከትንሽ ጊዜ በኋላም የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መነሳቱን ተከትሎ የጀርመን ናዚ ጦርን እንዲወጋ በሶቪየት ህብረት ተገዶ ዘምቷል።
ቀዩ ጦርን ተቀላቅሎ የናዚ ጦርን እየወጋ እያለም ለሶስተኛ ጊዜ የተማረከው ይህ ኮሪያዊ በአዶልፍ ሂትለር የሚመራው የጀርመን ጦር መልሶ የአሜሪካ እና እንግሊዝ ጦርን እንዲወጋ ወደ ጦር ግንባር ተልኳል።
የነ ጀርመን ቡድን በጦርነቱ በመሸነፉ ጦርነቱ ማብቃቱን ተከትሎ ህይወቱን በአሜሪካ ያደረገው ይህ ኮሪያዊ ከብዙ የጦር ግንባሮች በህይወት ተርፎ ህይወትን ሲያጣጥም ቆይቷል።
በመጨረሻም ይህ ወታደር የተዋጋላቸው ሀገራት ሁሉ ዜግነት የሰጡት ሲሆን በተወለደ በ92 ዓመቱ ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል።