የሩሲያ ፍርድ ቤት ጦርነትን ተቃውሟል ያለውን ወታደር የ6 ዓመት ገደማ እስር ፈረደበት
ካዛኪስታን ወታደሩን ባለፈው ዓመት መገባደጃ ላይ ለሩሲያ አሳልፋ ሰጥታለች
ወታደሩ ከእስራት በተጨማሪ የመኮንንነት ማዕረጉን ተነጥቋል
የሩሲያ- ዩክሬንን ጦርነት በመቃወም ሀገሩን ጥሎ ሸሽቷል የተባለው የሩሲያ የጸጥታ መኮንን በስድስት ዓመታት ተኩል እስራት መቀጣቱ ተነግሯል።
የ 36 ዓመቱ የፌደራል መከላከያ አገልግሎት ሻለቃ ሚካሂል ዚሊን ባለፈው ዓመት ሩሲያ የውትድርና ዘመቻ ስታወጅ ወደ ካዛኪስታን በህገ-ወጥ መንገድ ሸሽቶ ገብቷል ነው የተባለው።
የወታደሩ ባለቤትና እና ልጆቹ በህጋዊ የፍተሻ ኬላ በኩል ሩሲያን ለቀው መውጣታቸው ተነግሯል።
ካዛኪስታን ወታደሩን ባለፈው ዓመት መገባደጃ ላይ ለሩሲያ አሳልፋ ሰጥታለች።
ይህም አንድ መኮንን ሀገርን ጥሎ በመሸሽ ልዩ ፍርድ እንዲሰጥ አድርጓል ነው የተባለው።
ሮይተርስ የሩሲያ ዜና ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው በበርናኡል ከተማ የሚገኘው ፍርድ ቤት ዚሊን ሀገርን ጥሎ ቀመጥፋትና በህገ ወጥ መንገድ ድንበር በማቋረጥ ጥፋተኛ ሆኖ አግኝቶታል።
ፍርድ ቤቱ ከእስራት በተጨማሪ የመኮንንነት ማዕረጉን አንስቷል።
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሩሲያውያን ባለፈው ዓመት በተካሄደው ቅስቀሳ ምክንያት ከሀገራቸው ተሰደው ወደ ካዛኪስታን መግባታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
ነገር ግን ዚሊን ደህንነት ተቋም ውስጥ በመስራቱ ምስጢራዊ መረጃዎች ማግኘት ችሏል፤ እናም ሞስኮ ወታደሩን ለመመለስ ፍላጎት እንዳላት ቤተሰቦቹ ባለፈው ዓመት ለሮይተርስ ተናግረዋል።