በአሚሶም ስር የነበረ የኡጋንዳ ሰላም አስከባሪ ወታደር ሶስት ጓደኞቹን ገደለ
ኡጋንዳ አልሻባብን ለመዋጋት ከ2007 ጀምሮ ወታደሮቿን በሶማሊያ እንዳሰማራች ነው
ጓዶቹን የገደለው ወታደር የአእምሮ ችግር ሊኖርበት እንደሚችል ተገምቷል
አንድ ኡጋንዳዊ ወታደር አብረውት በተልእኮ ላይ የነበሩትን ሶስት ጓዶቹ ተኩሶ ገደለ፡፡
የተገደሉት ወታደሮች በሶማሊያ የተሰማራውን አፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል (አትሚስ) መሆናቸውም የኡጋንዳ ጦር አስታወቋል።
የኡጋንዳ ህዝብ መከላከያ ሃይል ቃል አቀባይ ብሪጅ ጄኔራል ፌሊክስ ኩላዪግይ ወታደሩ ሰኞ ማለዳ ከእንቅልፉ ከነቃ በኋላ በጓዶቹ ላይ "የጥይት ቀልሃ ማርከፍከፉ " ተናግረዋል።
አራቱም በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የሚጠብቀው ኃይል አካል ነበሩም ብለዋል ።
የኡጋንዳ ጦር የተኩስ መንስኤውን ለማወቅ የምርመራ ቦርድ አቋቁሟል ያሉት ቃል አቀባዩ፤ "ጓዶቹን ስለገደለው ወታደር ይህ ነው ለማለት ባንደፍርም ጭንቀት ወይም የአእምሮ ችግር ሊኖርበት እንደሚችል እናስባለን" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ወታደሩ በቁጥጥር ስር ውሎ ወደ ኡጋንዳ ወታደራዊ ወታደራዊ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብም ጭምር ገለጸዋል፡፡
በሶማሊያ የኡጋንዳ ወታደሮችን ያሳተፈ የመጨረሻው መሰል አሳዛኝ ድርጊት የተፈጸመው እንደፈረንጆቹ በግንቦት 2019 አንድ ወታደር እራሱን ከማጥፋቱ በፊት የበላይ መኮንኑን በጥይት የገደለበት አጋጣሚ እንደነበር አይዘነጋም።
ኡጋንዳ በሞቃዲሾ መንግስትን ለመጣል የሚንቀሳቀሱትን የሶማሊያ አማጺያን (አልሻባብ) ለመዋጋት ከ2007 ጀምሮ ወታደሮቿን በአፍሪካ ህብረት ተልእኮ ጥላ ስር በሶማሊያ እንዳሰማራች ነው፡፡
ኬንያ፣ ቡሩንዲ፣ ጅቡቲ እና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ ጋር በሶማሊያ ወታደሮቻቸው ያሰማሩ ሀገራት ናቸው፡፡