ከእሰራኤል ጋር በጁዶ ስፖርት ለምትፋለመው የሳዑዲ ተወካይ ከወዲሁ ድጋፍ እየጎረፈላት ነው
የሳዑዲ ዓረብያ የጁዶ ስፖርት ተጨዋቿ ታሃኒ አል-ቋህታኒ ከእሰራኤሏ ራዛ ሄርሾኮ ትጋጠማለች
የአረብ ሀገራት ስፖርተኞች ከእስራኤል ጋር ከሚደረግ ውድድር ራሳቸውን የሚያገሉ ቢሆንም፤ አል-ቋህታኒ እስካሁን ምንመ አላችም
ሳዑዲ ዓረብያ እና አስራኤል በቶኪዮ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች በጁዶ ስፖርት ፍልሚያ ሊፋጠጡ መሆኑ ተገለጸ።
ሳዑዲ ዓረብያ እና እስራኤል የሚፋጠጡት ደግሞ ሀገራቱን የወከሉ አትሌቶች በጁዶ ስፖርት በሚያደርጉት ውድድር ነው ተብለዋል።
ሳዑዲ ዓረብያን የምትወክለው የጁዶ ስፖርት ተጨዋቿ ታሃኒ አል-ቋህታኒ በ79 ኪሎ ምድብ ከእሰራኤሏ ተቀናቃኝ ራዛ ሄርሾኮ ለምታደርገው ግጥሚያ ከወዲሁ ድጋፍ እየጎረፈላት ነው፡፡
ወድድሩ የፊታችን ዓርብ የሚካሄድ ይሆናል።
ከዚህ በፊት ይደረግ እንደነበረው በሀገራቱ መካከል ባለው ታሪካዊ ቁርሾ ምክንያት የሳውዲ ዓረብያ ስፖርተኞች ከእስራኤላውያን ጋር ማንኛውም አይነት ውድድር የማያደርጉ ቢሆኑም አል-ቋህታኒ እስካሁን ራሷን ከውድድሩ ስለማግለል ያለችው ነገር የለም።
የሳዑዲ ደጋፊዎችምና ማህበራዊ ሚድያዎችም አል-ቋህታኒ ወደ ኋላ እንዳትል በማበረታታት ላይ ይገኛሉ።
የሳዑዲው የፖለቲካ ተንታኙ አል-ሃማድ የሳዑዲ ጀግናችን ከአስራኤላዊቷ ተጋጣሚ ላለመግጠም ወደ ኋላ እንደማታፈገፍግ ተስፋ አለኝ ሲል ተደምጠዋል።
"ይህ ስፖርት ነው፤ ከስፖርት ራስን በማግለል የምትጠፋ እስራኤል አትኖርም" ብሏል።