የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ድልን ተከትሎ ጄነራል አልቡርሃን ስልጣን እንዲለቁ እየተጠየቁ ነው
በጄነራል ሀሜቲ የሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የሱዳን ሁለተኛ ትልቅ ከተማ ይዟል
የሱዳን ጦር ያለከባድ ውጊያ ከተማውን በመልቀቁ የጦሩ አመራር ላይ ጥያቄ አስነስቷል
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ድልን ተከትሎ የሱዳን ጦር ዋና አዛዥ ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ስልጣን እንዲለቁ እየተጠየቁ ነው።
በጄነራል ሃምዳን ዳጋሎ ወይም ሀሜቲ የሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የሱዳን ሁለተኛ ትልቅ ከተማ ዋድ ማዳኒን መቆጣጠሩን ተከትሎ ነው የሱዳን ወተደራዊ መሪ ላይ ጫና መበርታት የጀመረው።
የሱዳን ፈጥኖ ደረሽ ኃይል ከተመዋን መያዝ የቻለው የሱዳን ጦርና ደጋፊዎቻቸው የተከፈተባቸውን ጥቃት መቀልበሳቸውን በመስመልከት ደስታውን ከገለጹ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።
የፈጥኖ ደረሽ ኃይል ድል ማድረጉን ተከትሎም የሱዳን ጦር ከዋድ ማድኒ ከተማ ያፈገፈገ ሲሆን፤ በሺዎች ዪቆጠሩ ተፈናቃዮች መኖሪያ የሆነችው ከተመዋን እና በርካታ ሲቪል ሰዎችን ለሱዳን ፈጥኖ ደረሽ ኃይል ትተው ወጥተዋ በሚል ወቀሳ ቀርቦባቸዋል።
የሱዳን ጦር በጉዳዩ ላይ በሰጠው ቁንጽል መግለጫ፤ ጦሩ ከተማዋን በፍጥነት ለቆ መውጣቱን አምኖ ምርመራ እንደሚደረግ ያስታወቀ ሲሆን፤ የከተማዋ ነዋሪዎች ግን ተጠያቂነት እንዲሰፍን እየጠየቁ ነው።
የከተማዋ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየትም፤ “እሁድ እለት የሱዳን ጦር ደል ማድረጉን ከሰራዊቱ ጋር ስናከብር ነበር፤ አሁን ግን ያ ሁሉ የድል ዜና ውሸት ነው” ብለዋል።
“ሁሉም የሱዳን ጦር አመራሮች ከስልጣናቸው ሊወገዱ ይገባል” ሲሉም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
በርካታ ሱዳናዊያን የሱዳን ጦር አዛዥ ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ስልጣን እንዲለቁ እየተጠየቁ ሲሆን፤ በአል ቡርሃ ቦታ አዲስ የሚተካው ሰው የፈጥኖ ደረሽ ኃይል ግስጋሴን ሊገታው ይችላል የሚል እምነት እንዳላቸውም ገልጸዋል።
ወታደራዊ ምንጮች እንዳስታወቁት፤ ከጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጋር ሆነው እየተዋጉ ያሉ ሌሎች የሱዳን ጦር አመራሮችም ውጊያው እየተካሄደበት ያለው መንገድ እንዳስቆጣቸው ተነግሯል።
እንደዚህ አይነት አለመግባባቶች ወደ በጦሩ ውስጥ የስልጣን ሽኩቻን ሊፈጥር እንደሚችል እና በዚህ መካከል የሚፈጠር ክፍተት የሱዳን ጦርን ሊያፈርሰው እንደሚችልም ስጋቶች ተቀምጠዋል።