ጦርነት ሱዳንን ወደ "መቅሰፍታዊ" ረሀብ እየመራት መሆኑ ተገለጸ
በጦርነት በደቀቀችው ካርቱም ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች በጥቂት የእለት ከእለት ምግቦች ቀናቸውን እየገፉ ናቸው
ተመድ እንደገለጸው 2/3 የሚሆነው የሀገሪቱ ህዝብ ወይም 30 ሚሊዮን ህዝብ የምግብ እርዳታ እንደሚፈልግ ገልጿል
ጦርነት ሱዳንን ወደ "መቅሰፍታዊ" ረሀብ እየመራት መሆኑ ተገለጸ።
በሱዳን፣ በጦርነት ቀጣና ወስጥ ያሉ ሰዎች በሚቀጥለው የበጋ ወቅት ከፍተኛ የረብ አደጋ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ተመድ አስጠንቅቋል።
በጦርነት በደቀቀችው ካርቱም ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች በጥቂት የእለት ከእለት ምግቦች ቀናቸውን እየገፉ ናቸው።
ተመድ እንደገለጸው 2/3 የሚሆነው የሀገሪቱ ህዝብ ወይም 30 ሚሊዮን ህዝብ የምግብ እርዳታ እንደሚፈልግ ገልጿል። እንደ ተመድ ከሆነ ይህ ቁጥር በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች እና በሱዳን ጦር መካከል ግጭት ከመቀስቀሱ ከሚያዝያ አጋማሽ በፊት ከነበረው በእጥፍ ጨምሯል።
በሀገሪቱ የምርት ወቅት 18 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ እርዳታ እንደሚፈልጉ ተመድ ገልጿል።
በተወሰነ የሀገሪቱ ክፍል 20 በመቶ የሚሆነው ቤተሰብ መቅሰፍታዊ ለሆነ የረሀብ አደጋ መጋለጡን ተከትሎ የረሀብ አደጋ በመንግስት ታውጇል።
የደብሊውኤፍፒ ካንትሪ ዳይሬክር ኢዲ ሮዌ "ብዙ ቀጥር ያላቸው ሰዎች የእለት ምግባቸውን ለማግኘት እየታገሉ ነው፤ ነገሮች ካልተቀየሩ ይህን ማድረግ የማይችሉበት ከባድ አደጋ አለ" ብለዋል።
ጦርነቱ የሱዳን ዋና ከተማ ከርቱምን አውድሟል፤ በዳርፉር የጎሳ ግጭት ተቀስቅሶ ግድያ እንዲፈጸም ምክንያት ሆኗል።
ሁለቱ የጦርነቱ ተፋላሚዎች እርዳታ ለተጎጅዎች እንዳይደርስ በማስተጓጎል እርስበርሳቸው ይካሰሳሉ።