የሱዳን ጦር ቁልፍ ከሆነችው ከተማ ለቆ መውጣቱን አስታወቀ
አይኦኤም ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ወደ ከተማዋ መግባታቸው 300ሺ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል ብሏል
የሱዳን ጦር ከተማዋን ለቆ የወጣው በጀነራል መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ የሚመሩት ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ወደ ከተማዋ መጠጋታቸውን ተከትሎ ነው
የሱዳን ጦር ቁልፍ ከሆነችው ከተማ ለቆ መውጣቱን አስታወቀ።
የሱዳን ጦር ቁልፍ የሆነችውን የዋድ መዳኒ ከተማ ለቆ መውጣቱን በትናንትናው እለት አስታውቋል።
የሱዳን ጦር ከተማዋን ለቆ የወጣው ተቃናቃኝ የሆኑት በጀነራል መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ የሚመሩት ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ወደ ከተማዋ መጠጋታቸውን ተከትሎ ነው።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ወደ ከተማ ሲጠጉ በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ግጭት ሸሽተው የመጡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሱዳናውያን ጓዛቸውን ጠቅልለው በድጋሚ ተሰደዋል።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በዳርፉር ሰፊ ቦታ እና ከካርቱም በስተምስራቅ በኩል አዳዲዝ ግዛቶችን በመያዝ ባለፉት ሳምንታት ድል እየቀናቸው መሆኑ ተገልጿል።
ዋድ መዳኒ እንደ እርዳታ ማዕከል እና ለሀገር ውስጥ ስደተኞች መጠለያነት ስታገለግል የቆየች ከካርቱም 170 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ወሳኝ ከተማ ነች።
አለምአቀፉ የስደተኞች ድርድት(አይኦኤም) ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ወደ ከተማዋ መግባታቸው 300ሺ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል ብሏል።
በከተማ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ተሰራጭተው እንደሚገኙ እና የሱዳን ጦር የአየር ጥቃት እያደረሰ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሱዳን ባለፉት ሁለት አስርት አመታት በዳርፉር ያሉ ታጣቂዎችን እዲያጠቁላት ያስታጠቀቻቸው ከሚሊሻነት ወደ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ያደጉት ተዋጊዎች አብዛኛውን የካርቱም ክፍል ተቆጣጥረዋል።
በሱዳን ያለውን ግጭት ለመፍታት በተለይም ተስፋ ተደርጎበት የነበረው በአሜሪካ እና በሳኡዲ አረቢያ አመቻችነት በጂዳ ሲደረግ የነበረው ድርድር መቋረጡ ይታወሳል።
አሜሪካ ሁለቱም ተፋላሚ ኃይሎች የጦር ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ውሳኔ አሳልፋለች።