የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አል ቡርሃን ወደ ኤርትራ አቀኑ
የሽግግር ምክርቤቱ ጀነራሉ በሱዳን የእርስበርስ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ዋና መቀመጫ ካደረጓት ፖርት ሱዳን ሲሸኙ የሚያሳይ ምስል ለቋል
ጀነራል አልቡርሃን ወደ ኤርትራ ያቀኑት የደህንነት ኃላፊውን አውል አህመድ ኢብራሂም ሞፋዚልን አስከትለው ነው
የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክርቤት ፕሬዝደንት እና የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አልቡርሃን በዛሬው እለት ወደ ኤርትራ አቅንተዋል።
የሽግግር ምክርቤቱ ጀነራሉ በሱዳን የእርስበርስ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ዋና መቀመጫ ካደረጓት ፖርት ሱዳን ሲሸኙ የሚያሳይ ምስል ለቋል።
አል ቡርሃን በኤርትራ በሚኖራቸው ቆይታ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ጋር ወይይት ያደረጋሉ ብሏል ምክር ቤቱ።
ጀነራል አልቡርሃን ወደ ኤርትራ ያቀኑት የባህልና ሚዲያ ሚኒስትሩን ካሊድ አል አሰር እና የደህንነት ኃላፊውን አውል አህመድ ኢብራሂም ሞፋዚልን አስከትለው ነው።
በሱዳን፣ ጀነራል አልቡርሃን እና ጀነራል ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ በሚመሯቸው ጦሮች መካከል የተጀመረው ጦርነት 2 1/2 በላይ አመት አስቅጥሯል።
ጀነራሎቹ ወደ ጦርነት የገቡት ከአልበሽር ውድቀት በኋላ የሱዳንን ሽግግር ይመራሉ ተብለው በተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብዳለ ሀምዶክ ላይ መፈንቀል መንግስት ካደረጉ በኋላ ነበር።
በጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን እና ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ በሀገር ውስጥ አለያም ድንበር አቋርጠው ወደ ሌሎች ሀገራት መሰደዳቸውን አለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) መግለጹ ይታወሳል።