የኢትዮጵያ ተሽከርካሪዎች ጋዝ ወደ ኢትዮጵያ እንዲያስገቡ መፍቀዷን ካርቱም አስታውቀለች
ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ጋዝ እንዲገባ ፈቀደች፡፡
የሱዳን ጦር አዛዥ ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋዝ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ መፍቀዳቸውን የአገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡
እንደዘገባዎቹ ከሆነ ካርቱም ተሽከርካሪዎች ከኢትዮጵያ በምትዋሰንበት በገላባት በኩል እንዲገቡና ጭነው እንዲወጡ ፈቅዳለች፡፡
የሱዳን መንግስት ንብረት የሆነው ናይል ፔትሮሊየም ነው የጋዝ ምርቶችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲያስገባ የተፈቀደለት፡፡
አል ዐይን አማርኛም በአዲስ አበባ የሚገኘውን የድርጅቱን ቢሮ በመጠየቅ ይህንኑ አረጋግጧል፡፡
ቢሮው የጋዝ ምርቶችን በጋላባት በኩል ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት እንደተፈቀደለት ለአል ዐይን አስታውቋል፡፡
ናይል ፔትሮሊየም ምርቶቹን ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ለመኖሪያ ቤቶች እና ለንግድ ተቋማት በወኪሎች በኩል እንደሚያከፋፍል ተገልጿል፡፡