የሱዳን ጦር በዋና የጦር ማዘዣው ላይ ጥቃት ሊያደርሱ የነበሩ ድሮኖችን መትቶ መጣሉ ተገለጸ
ከተቀሰቀሰ አንድ አመት በሆነው ጦርነት ውስጥ ሁለቱም ተፋላሚዎች ድሮን እየተጠቀሙ ናቸው
የሱዳን ጦር በዛሬዉ እለት በሸዲ በሚገኘው ዋና የጦር ማዘዣው ላይ ጥቃት ሊያደርሱ የነበሩ ድሮኖችን በጸረ-ጄት ሚሳይሎች መትቶ መጣሉን ገልጿል
የሱዳን ጦር በዋና የጦር ማዘዣው ላይ ጥቃት ሊያደርሱ የነበሩ ድሮኖችን መትቶ መጣሉ ተገልጿል።
የሱዳን ጦር በዛሬዉ እለት በሸዲ በሚገኘው ዋና የጦር ማዘዣው ላይ ጥቃት ሊያደርሱ የነበሩ ድሮኖችን በጸረ-ጄት ሚሳይሎች መትቶ መጣሉን ሮይተርስ የአይን እማኞችን እና ወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
የጦር ማዘዣው ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት ቢሰነዘርበትም፣ የትኛውም ድሮን ኢላማውን መምታት እንዳልቻለ የሱዳን ጦር ምንጮች መግለጻቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
የሱዳን ጦር አዛዥ ጀነራል አብደል ፋታህ አልቡርሃን ከካርቱም በሰሜን አቅጣጫ 180 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሸዲ ሰኞ እለት መድረሳቸውን የሱዳን ጦር ሚዲያዎች ዘግበው ነበር። ጀነራሉ ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት በሸዲ ስለመኖራቸው የታወቀ ነገር የለም።
የሱዳን ጦር ሰፊዋን የሰሜን አፍሪካ ሀገር ለመቆጣጠር ከተቀናቃኙ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጋር እየተዋጋ ይገኛል።
የማክሰኞው የድሮን ጥቃት በጦሩ ቁጥጥር ስር ባሉ ቦታዎች ላይ ሲደረግ ለሶስተኛ ጊዜ ነው ተብሏል። የአትባራ ከተማ፣ የናይል ወንዝ ግዛት እና በምስራው የምትገኘው የገዳሪፍ ግዛት የድሮን ጥቃት ደርሶባቸዋል።
ከተቀሰቀሰ አንድ አመት በሆነው ጦርነት ውስጥ ሁለቱም ተፋላሚዎች ድሮን እየተጠቀሙ ናቸው።
አብዛኛውን የካርቱም ከተማ እና የሀገሪቱን ምዕራባዊ ክፍል የተቆጣጠረው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጦር ለእነዚህ ጥቃቶች ኃላፊት አልወሰደም።
አጋር በነበሩት የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አልቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎችን በሚመሩት ጀነራል መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ መካከል የተፈጠረው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን እንዲገደሉ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል።