የሱዳን ተቃዋሚዎች አልቡርሃን ስልጣን እለቃለሁ ማለታቸው “ጊዜያዊ ማፈግፈጊያ ነው” አሉ
አል ቡርሃን ስልጣን ለሲቪል አስተዳድር እንደሚያስረክቡ ገልጸዋል
የሱዳን ሰልፈኞች በአል ቡርሃን በሚመራው መንግስት ላይ ጫና ማሳደራቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል
የሱዳን ተቃዋሚዎች፤ የሀገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና የጦር ኃይሎች አዛዥ ሌ/ጄነራል አብደል ፋታህ አልቡርሃን ስልጣንን ለሲቪል አስተዳደር አስረክባለሁ ማለታቸው ጊዜያዊ ማፈግፈጊያ መሆኑን ገለጹ።
የሀገሪቱ ሰልፈኞች በአል ቡርሃን በሚመራው መንግስት ላይ ጫና ማሳደራቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። ዋነኛው የሱዳን ተቃውሞ መሪ የነጻነትና የለውጥ ኃይሎች ዛሬ እንዳስታወቀው ተጨማሪ ሰልፎች እንዲደረጉ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
የነጻነትና ለውጥ ኃይሎች በቀጣይ ተጨመሪ ሰልፎች እንዲደረጉ ጥሪ ያቀረበው ሌፍተናንት ጀነራል አልቡርሃን ስልጣን ለሲቪል አስተዳድር እንደሚያስረክቡ ከገለጹ በኋላ ነው ተብሏል።
የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ም/ቤት ፕሬዝዳንት አብዳላህ የሽግግር መንግስቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክን ከስልጣን በማውረድ ሙሉ የመንግስትን ስልጣን መቆጣጠሩ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎም በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት የተቃውሞ ሰልፎች በመካሄዳቸው፤ አልቡርሃን ለነዚህ ሰልፎች ይሆናል በሚል ዛሬ የሰጡት ስልጣንን ለሲቪል አስረክባከሁ ምላሽም በነጻነትና የለውጥ ኃይሎች ውድቅ መደረጉ ተሰምቷል።
በቅርቡ ሱዳናውያን ችግሮቻቸውን ለመፍታት ያስችላል ያሉትን ንግግር ቢጀምሩም የአፍሪካ ህብረት ግን ግልጸኝነት እንደሚጎድለው በመግለጽ ራሱን ከንግግሩ ማግለሉ ይታወሳል።
የቀድሞው የሱዳን መሪ ኦማር ሃሰን አልበሽር ከስልጣን ተወግደው በሀገሪቱ ሽግግርና ለውጥ እንደሚመጣ ተስፋ ቢደረግም አሁንም ካርቱም ጎዳናዋ የሰልፈኞች ሆኗል፡፡
በቀጣይ በሚደረጉ የፖለቲከኞች ውይይት ላይም ወታደራዊ አመራሩ እንደማይሳተፍ ጀነራል አልቡርሃን ቢጠቅሱም መቼ ለሲቪል አስተዳድሩ እንደሚስረክቡ ግን አልጠቀሱም።
ውስጣዊ ችግር ላይ ካለችው ሀገራቸው ወደ ናይሮቢ ያቀኑት ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን፤ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ተገናኝተዋል።