ሱዳን በተመድ የፀጥታው ም/ቤት ስብሰባ ላይ ስለ ኢትዮጵያ ምን አለችʔ
የሱዳን መንግስት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የፈጥኖ ደረሽ ኃይሉ ላይ ጫና እንዲፈጥር ጥሪ አቅርቧል
በተመድ የፀጥታው ም/ቤት ተወካይ ጦርነቱን አስመልክቶ በሰጡት ማብራያ ላይ ስለ ኢትዮጵያ ተናግረዋል
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የሱዳን ተወካይ በሀገሪቱ ባለው ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የሱዳን ተወካይ አል ሀሪስ ኢድሪስ በስብሰባው ላይ፤ በሱዳን ሰሜናዊ ክፍል ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት አካባቢ ስላለው ሁኔታ አንስተዋል።
በዚህም የሱዳን ጦርና አር.ኤስ.ኤፍ መካከል ጦርነት ከተከሰተ ወዲህ ሱዳን በሰሜን በኩል ከኢትዮያ ጋር በሚያዋስናት አካባቢ የተረጋጋ መሆኑን ምንም ችግር እንዳልተከሰተበት እና የተረጋጋ መሆኑን አስታውቀዋል።
ተወካዩ ኢትዮጵያ ድንበሯን ጦርነቱን ሸሽተው ለተሰደዱ ሱዳናውያን ድንበሯን ከፍታ መቀበሏንም ጭምር አስታውቀዋል።
በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የሱዳን ተወካይ አል ሀሪስ ኢድሪስ አክለውም ቻድ በድንበሯ ላይ የፈጥኖ ደራሽ ኃይል አማጽያንን አስራለች ሲሉም ተናግረዋል።
ጦርነቱን ተከትሎ ጦርነቱን ሸሽተው የተሰደዱ 113 ሺህ ሱዳናውያን ቻድ ደርሰዋል ያሉት ቃል አቀባዩ፤ ከዳርፉር የተፈናቀሉ 350 ሺህ ሱዳናውያን በሀገር ውስጥ መጠለያ ካምፖች ውስጥ ይገኛሉ ብለዋል።
ለፈጥኖ ደረሽ ኃይሉ የፀረ አውሮፕላን የጦር መሳሪዎች በብዛት በድብቅ እየተላለፉ እንደሆነ ደርሰንበታል ሲሉም ተወካዩ ተናግረዋል።
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በኤል ጄኒና፣ በዛሊየንጊ እና ናይላ በተባሉ ስፍራዎች የሚያፈጽመውን ጥቃት ቀጥሎበታል ሲሉ ተናግረዋል።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በፈጥኖ ደራሽ ኃይል ላይ ጫና እንዲያሳድር የጠየቁት የሱዳን የተመድ ተወካይ፤ ታጣቂ ኃይሉ ማስታጠቅ እንዲቆም ማእቀብ እንዲጣልም ተማጽነዋል።