ሱዳን የብድር እፎይታ ለማግኘት የገንዘቧን ዋጋ በከፍተኛ መጠን ቀነሰች
ባንኩ ለውጡን ያደረገው የባንክ ምንዛሬን ከጥቁር ገበያ ጋር አንድ ለማድረግ ጭምር ነው ተብሏል
የአንድ አሜሪካን ዶላር ምንዛሬ ዋጋ ከ55 የሰዱን ፓውንድ ወደ 375 የሱዳን ፖውንድ አሻቅባል
የሱዳን ማእከላዊ ባንክ እንዳስታወቀው በባንክና በጥቁር ገበያ ያለውን የገንዘብ ምንዛሬ አንድ ለማድረግ፣የኢኮኖሚ ቀውሱን ለመቅረፍና የብድር እፎይታ ለማግኘት የሱዳንን መገበያያ ገንዘብ(ፓውንድ) ዋጋ በከፍተኛ መጠን ቀንሷል፡፡
የተደረገው ለውጥ የውጭ ለጋሾችና ኢንተርናሽናል ሞናተሪ ፈንድ (አይኤምኤፍ) ከሚፈልጉት ለውጥ ውስጥ ቁልፍ የሚባል ነው፤ ነገርግን የመሰረታዊ የምግብ እጥረትና ፈጣን የኑሮ ውድነት የሀገሪቱን ያልረጋ ፖለቲካ በማወሳሰቡ ለውጡ ለወራት ዘግይቷል፡፡
ማእከላዊ ባንኩ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ375 የሱዳን ፓውንድ እንዲመነዘር መወሰኑን መርካታ ባንኮች የገለጹ ሲሆን ቀደም ሲል አንድ ዶላር በ55 ፓውንድ በባንክ ይመነዘር ነበር፡፡ በቅርቡ በጥቁር ገበያ አንድ ዶላር ከ350 እስከ 400 የሱዳን ፖውንድ ይመነዘር ነበር፡፡
ማእከላዊ ባንኩ የየእለቱን የምንዛሬ መጠን መግለጫ ወደ ሁሉም ባንኮች ይልካል፡፡ባንኮችና የልውውጥ ቢሮዎች ማእከላዊ ባንኩ ካስቀመጠው 5 በመቶ በላይ ወይም በታች መገበያየት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ ከማእከላዊ ባንክ የሚላከው መግለጫ በገንዘብ ልውውጥ ማለትም በሽያጭ ወይም በግዥ የሚገኘው ትርፍ መጠን ከ0.5 በመቶ በላይ መሆን የለበትም ይላል፡፡
የማእከላዊ ባንክ የገንዘብ ምንዛሬን እንደማይቆጣጠር የባንኩ ገዥ ቢናገሩም የፋይናንስ ሚኒስትሩ ጂብሪል ኢብራሂም ምንጫቸው ያልተጠቀሰ የውጭ ፈንድ ወደ ሱዳን መግባቱንና፤አስፈላጊ ሲሆን ማእከላዊ ባንክ ጣልቃ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የማእከላዊ ባንክ ፕሬዘዳንት ሞሃመድ አልፋቲህ ዜይንላባዲኔ ወሳኔው የማጋሸብ ሳይሆን እንደሁኔታው የሚወሰድ ቁጥጥር ነው ብለዋል፡፡ አዲሱ የፓውንድ ምንዛሬ ምጥነት ከተወሰነ በኋላ ወሳኝ የሆኑ ሸቀጦች የመለየት ስራ መሰራቱንና አስፈላጊ ያልሆኑ እቃቆችን የውጭ ግዥ ገደብ መጣሉ ተገልጿል፡፡
በአይኤምኤፍ ግምገማ መሰራት ሱዳን የ60 ቢሊዮን ዶላር የብድር እፍሮታ ለማግኘት ባለፈው አመት መጨረሻ ላይ የተጠበቀ ቢሆንም በፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ሳይፈጸም ቆይቷል፡፡