የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክና የተቃዋሚ ቡድኑ መሪ በአዲስ አበባ ስምምነት ላይ ደረሱ
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክና የተቃዋሚ ቡድኑ መሪ በአዲስ አበባ ስምምነት ላይ ደረሱ
የሱዳን መንግስትና ተቃዋሚ ቡድን በአዲስ አበባ ሲያካሄዱት በነበረው ድርድር ላይ በስድስት መርሆች ላይ ከስምምነት ደርሰዋል፡፡
በሱዳን መንግስት በኩል የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ከሱዳን ህዝብ ነጻ አውጭ ንቅናቄ የሰሜኑ ክንፍ (SPLM-N) መሪ ከሆኑት አብዱልአዚዝ አልሂሉ ጋር በመርሆቹ ላይ የስምምነት ፊርማቸውን በትናንትናው እለት አኑረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ከትናንት በስትያ አዲስ አበባ የመጡት የሱዳን መንግስት ከንቅናቄው መሪ ጋር በጁባ ሲያካሂደው የነበረው ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ነበር፡፡
የንቅናቄው መሪ በጁባ ሲካሄድ የነበረውን ድርድር ካቋረጡ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቸው ይታወሳል፡፡
ይህ የንቅናቄ ቡድን በሱዳን ብሉናይል እና ደቡብ ኮርዶፋን ግዛቶች የሚንቀሳቀስ ነው፡፡
መንግስትና የንቅናቄው የተስማሙባቸው ስድስት ነጥቦች
-ሱዳን የብዙ ዘር፣ ብሄር፣ ብዙ ሀይማኖቶችና ብዙ ባህል ያላት ሀገርመሆኗን መቀበል፡፡ ለእነዚህ ብዙሃነት እውቅና መስጠት
-የፖለቲካና የማህበራዊ እኩልነቶች በህግ ዋስታና እንዲያገኙ ማድረግ
-በሱዳን የዲሞክራሲ መንግስት መመስረት፡፡ሱዳን ዲሞክራሲ የሰፈነባት የሁሉም ዜጋ መብት የተከበረባት ሀገር እንድትሆን መንግስትና ሀይማኖት እንዲለያዩ እንዲደረግና ዜጎችች በእምነታቸው ምክንያት እንዳይገለሉ፡፡
- የኑባ ማውንቴንና ብሉናይል የጸጥታ አደላደል ላይ ስምምነት እስከሚደረስና የመንግስትና የሀይማኖት መለያየት ተግባራዊ እስከሚሆን ድረስአሁን ባሉበት ራሳቸውን የመከላከል መብታቸው እንዲጠበቅ
-የጸጥታ ስምምነቱ እስከሚደረስ ድረስና በሰላም ስምምነቱ ሂደት ግጭት ለማቆም
- በተለያዩ ሰዱን ህዝቦች መካከል ፍትሃዊ የሆነ የስልጣንና የሀበት ክፍፍል በህገመንገስቱ ማረጋገጥ
የኢትዮጵያ መንስግትና ሌሎች አካላት የሱዳን መንግስትና የተቃዋሚ ቡድን በአዲስ አበባ እንዲደራደሩ ማመቻቸታቸው ታውቋል፡፡