ሱዳን ከኢትዮጵያ በሚያዋስናት ብሉናይል ግዛት ባሉ ሁለት ከተሞች ሰአት እላፊ ገደብ ጣለች
የሱዳን ባለስልጣናት በብሉናይል በሚገኙ ሁለት ከተሞች የተከሰተውን ደም አፋሳሽ ግጭት ተከትሎ በከተሞቹ የሰአት እላፊ ገደብ ጣለች።
ለኢትዮጵያ አዋሳኝ በሆነዉ የብሉናይል ግዛት በተነሳ እና ለቀናት በቆየው ግጭት 31ሰዎች መገደላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። የብሉናይል ግዛት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው አንድ አርሶአደር መገደሉን ተከትሎ የተፈጠረው ግጭት ወደ በርካታ ከተሞች ሊስፋፋ ችሏል። ነገርግን የጸጥታ ኃይሎች ግጭቱን ተቆጣጥረውታሎ ብሏል።
መግለጫው እንደገለጸው በግጭቱ 36 ሰዎች ቆስለዋል፤ 16 ሱቆች ወድመዋል። በግጭቱ ምክንያት በዳምዚን እና ሮዚረስ ከተሞች የሰአት እላፊ ገደብ መጣሉን መግለጫው አስታውቋል።
ነገርግን ሮይተርስ አናገርኳቸው ያላቸው ነዋሪዎች ግጭቱ ቅዳሜ እለትም መቀጠሉን እና የጸጥታ ኃይል አለመድረሱንም ተናግረዋል።
የሱዳን የዶክተሮች ማእከላዊ ኮሚቴ እንዳስታወቀው ብዙ ቁስለኞች ወደ ሁለቱ ከተሞች እየደረሱ ነው።
ምንም እንኳን በፈረንጆቹ 2020 በተወሰኑ አማጺያን ሀገር አቀፍ የሰላም ስምምነት ቢፈረምም፣ በሱዳን የምስራቅ ጫፍ እና ምእራብ ዳርፉርን ጨምሮ በበርካታ ግዛቶች አልፎ ከልፎ ግጭቶች እየተከሰቱ ናቸው።
ሱዳንን እያስተዳደረ ያለው ወታደራዊ መንግስት ስልጣኑን ለሲቪል እንዲያስረክብ የሚጠይቁ ተቃውሞዎች በተለያየ ጊዜ ይስተዋላሉ።