የሱዳኑ መሪ ወታደራዊ ፍጥጫውን ለማስወገድ የሚረዳ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነኝ አሉ
የሲቪል መንግስት ይቋቋም የሚል ጥያቄ የሚያንጸባርቁ ሰልፎች በተጋጋሚ መደረጋቸው ይታወሳል
የሱዳን ሰራዊት የአርኤስኤፍ እንቅስቃሴ ከፈቃዱ ውጭ መሆኑን ገልጿል
የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ ጀነራል አል ቡርሃን በጀነራል ሀምዳን ደጋሎ ከሚመራው ራፒድ ሰፖርት ፎርስ(አርኤስኤፍ) ጋር የገቡት ፍጥጫ እንዲወገድ ማንኛውንም እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ፍጥጫው የተፈጠረው በጀነራል ሀምዳን ደጋሎ የሚመራው አርኤስኤፍ ወደ ሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም እና ወደ ሌሎች ከተሞች መሰማራቱን ተከትሎ ነበር።
የሱዳኑ መሪና የጦር አዛዥ ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ከኃይለኛው የፓራሚሊታሪ ራፒድ ደጋፊ ሃይሎች ጋር እየተካሄደ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ማንኛውንም እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅተዋል።
"ችግሩ እየቀረፈ መሆኑን ለዜጎች እናረጋግጣለን።" ብለዋል ቡርሃን ዛሬ በሰጡት መግለጫ።
በሠራዊቱ እና በአርኤስኤፍ መካከል ያለው ውጥረት ሐሙስ እለት የተባባሰው፣አርኤስኤፍ የተወሰኑ ሀይሉን በሰሜናዊ ከተማ ሜሮዌ ወደሚገኝ ወታደራዊ አየር ማረፊያ አካባቢ ካዘዋወረ በኋላ ነበር።
የሱዳን ሰራዊት የአርኤስኤፍ እንቅስቃሴ ከፈቃዱ ውጭ መሆኑን ገልጿል።
የሱዳን ወታደራዊ መሪ የሲቪል ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩት አብደላ ሀዶክ ላይ መፈንቅለ መንግስት አድርጎ ሀገሪቱን ወደማያባራ ቀውስ ውስጥ ከቷታል።
የሲቪል መንግስት ይቋቋም የሚል ጥያቄ የሚያንጸባርቁ ሰልፎች በተጋጋሚ መደረጋቸው ይታወሳል።