የሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች ስምምነት ለአንድ ሳምንት ተራዘመ
ቅዳሜ ይፈረማል የተባለው ስምምነት "በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ መግባባት ባለመኖሩ" ዘግይቷል ተብሏል
የሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ወታደራዊ ኃይሎች ሲቪል መንግስት ለመመስረት ባለፈው ታህሳስ ላይ ተስማምተው ነበር
የሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች ስምምነት ለአንድ ሳምንት ተራዘመ ፡፡
በሱዳን ሲቪል መንግስት ለመሰየም እና አዲስ ሽግግር ለመጀመር ሊካሄድ የነበረው የስምምነት ፊርማ እስከ የሚቀጥለው ሳምንት ዘግይቷል።
ሮይተርስ የድርድሩን ቃል አቀባይ ጠቅሶ እንደዘገበው ወታደራዊ እና ሲቪል ፓርቲዎች ስምምነቱን ለማራዘም ተስማምተዋል።
በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል እና ሱዳን ጦር መካከል አለመስማማት መኖሩ ተገለጸ
“ቀሪ መሰናክሎችን በጥቂት ቀናት ውስጥ ተወያይተው ለመፍታት እና የመጨረሻውን የፖለቲካ ምምነት በሚያዝያ ስድስት ለመፈራረም ተስማምተዋል" ብለዋል።
ስምምነቱ ትናንት ቅዳሜ ለመፈረም ታቅዶ የነበረ ቢሆንም "በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ መግባባት ባለመኖሩ ዘግይቷል" ሲሉ ቃል አቀባዩ ካሊድ ኦማር የሱፍ ተናግረዋል።
በዚህ ሳምንት የሀገሪቱን የፈጣን ድጋፍ ሰጭ ኃይሎችን ወደ ወታደራዊው አካል ለማዋሃድ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ ላይ አለመግባባቶች ተፈጥሯል ነው የተባለው።
የሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ወታደራዊ ኃይሎች ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ ለሁለት ዓመታት የሚቆይ ሲቪል መንግስት ለመመስረት ባለፈው ታህሳስ መስማማታቸው ይታወሳል።
የማዕቀፍ ስምምነቱ በፈረንጆች 2021 በመፈንቅለ መንግስት የተቀሰቀሰውን የሀገሪቱን ብጥብጥ ያቆማል የሚል ተስፋን የሰነቀ ነው።