ስምምነቱን “ለአሜሪካና ለመላው አለም ትልቅ ድል ነው” ብለዋል ትራምፕ
ስምምነቱን “ለአሜሪካና ለመላው አለም ትልቅ ድል ነው” ብለዋል ትራምፕ
ሱዳን ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት ላይ መድረሷን የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታውቀዋል፡፡
ስምምነቱን “ለአሜሪካና ለመላው አለም ትልቅ ድል ነው” ሲሉ ትራምፕ አድንቀውታል፡ሱዳን ከተባበሬት አረብ ኤምሬትና ከባህሬን ቀጥሎ ከእስራኤል ጋር ስምምነት በመፈረም ሶስተኛዋ የአረብ ሀገር ሆናለች፡፡
ፕሬዘዳንት ትራምፕ ሎሌች የአረብ ሀገራትም ከእስራኤል ጋር ስምምነት ይፈርማሉ ብለዋል፡፡
ከስምምነቱ በኋላ ሱዳን አሜሪካ እስራኤል የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክርቤት ፕሬዘዳንት አልቡርሃን፣ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኒታኒያሁ ሱዳን ወደ ዲሞክራሲ በምታደረገው ታሪካዊ መሻሻልና በቀጣናው ሰላምን ማስፈን በሚቻልበት ሁኔታ መክረዋል፡፡
መግለጫው በአምባገነን መንግስት ስር መከራው ሲያይ የቆየ የሱዳን ህዝብ አሁን ኃላፊነት ተረክቧል፤ የሸግግር መንግስቱ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ወኔ አግኝቷል፤የዲሞክረሲ ተቋማትም እየገነባ ነው፤ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት አሻሽሏል ብሏል፡፡
አሜሪካና እስራኤልም ከአጋሮቻቸው ጋር በመሆን የሰዱን ህዝብ የጀመረውን ዲሞክራሲ ተቋማት ግንባታ፤ሽብርን በመዋጋትና በሌሎችም ለማገዝ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
“ከዚህ ታሪካዊ ለውጥ አንፃር እና ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሱዳንን ሽብርተኝነትን ከሚደግፉ መንግስታት ዝርዝር ውስጥ ለማስወጣት ከወሰኑ በኋላ አሜሪካ እና እስራኤል በአዲስ ጅምር ከሱዳን ጋር አጋርነት ለመመስረት እና ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ሙሉ ውህደቷን ለማረጋገጥ ተስማምተዋል” ሲልም መግለጫው ያትታል፡፡
ሱዳን በአሜሪካ የሽብርተኝነት ደጋፊ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ በመካተቷ ምክንያት እ.ኤ.አ. ከ 1993 ጀምሮ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ተጥሎባት ቆይታለች፡፡
የጋራ መግለጫው አሜሪካ የሱዳንን ሉዓላዊነት ወደነበረበት ለመመለስ እና የሀገሪቱን የዕዳ ጫና ለመቀነስ ዓለም አቀፍ አጋሮችን የሚያሳትፉ እርምጃዎችን እንደምትወስድ ጠቁሟል ፣ ይህም የዕዳ ስረዛ ውይይቶችን እንደሚያካትትም ተገልጿል፡፡