ፖለቲካ
የሱዳን ጦር መሪ አልቡርሃን ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ውጭ አቀኑ
በጦርነቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ሀገራቸውን ጥለው ሲሰደዱ በሚሊዮን የሚቆጠሩት ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል
አልቡርሃን ካሃዲ ያሏቸው ኃይሎች መሸነፍ እንዳለባቸው እና ከእዚህ ጋር መነጋገር አስቸጋሪ እንደሆነም ገልጸዋል
የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አልቡርሃን በሀገሪቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ውጭ አቅንተዋል።
የሱዳን ጦር መሪ እና የሱዳን የሽግግር ሉአላዊ ምክርቤት ኘሬዝደንት አልቡርሃን የመጀመሪያ በሚሆነው ጉብኝታቸው ወደ ግብጽ አቅንተዋል።
ምክርቤቱ ባወጣው መግለጫ አልቡርሃን በግብጹ ከፕሬዝደንት አልሲሲ ጋር እንደሚገናኙ ገልጿል።
ምክርቤቱ እንደገለጸው በዛሬው እለት ወደ ግብጽ ያቀኑት የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አልቡርሃን በግብጿ ኢል አላሚን ከተማ ከፕሬዝደንት አልሲሲ ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ።
በሱዳን፣በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ባለፈው ሚያዝያ ወር ወዲህ አልቡርሃን ወደ ውጭ ሲወጡ ይህ የመጀመሪያቸው ነው።
አልቡርሃን ካሃዲ ያሏቸው ኃይሎች መሸነፍ እንዳለባቸው እና ከእዚህ ጋር መነጋገር አስቸጋሪ እንደሆነም ገልጸዋል።
አልቡርሃን ይህን ያሉት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በዘላቂነት ተኩስ ለማቆም እና በሱዳን የወደፊት እጣፋንታ ላይ ለመነጋገር ዝግጁነቱን መግለጹን ተከትሎ ነው።
በጦርነቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ሀገራቸውን ጥለው ሲሰደዱ በሚሊዮን የሚቆጠሩት ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።