በሱዳን አንድ ወቅት አጋር በነበሩት የሱዳን ጦር መሪ በጀነራል አልቡርሃን እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይልን በሚመሩት ጀነራል ሄሜቲ መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ነው
በሱዳን በተፋላሚዎች መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት 23 ሰዎች በድሮን መገደላቸው ተገልጿል።
- የኤለን መስክን ትኩረት ለማግኘት ኤክስን የጠለፈው “አኖኒመስ ሱዳን”
- የሱዳን ጦር አዛዥ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከካርቱም ወጥተው የጦር ሰፈሮችን ጎበኙ
በዛሬው እለት በካርቱም በሚገኝ ክፍት የገበያ ቦታ ላይ በድሮን ተካሃዷል በተባለ የድሮን ድብደባ 23 ሰዎች መገደላቸውን አክቲቪስቶች እና የህክምና ባለሙያዎች መናገራቸውን ኤፒ ዘግቧል።
በጥቃቱ 30 የሚደርሱ ሰዎች የመቁሰል አደጋ እንደረሰባቸው ሪዚስታንስ ኮሚቴ የተባለው የአክቲቪስት ቡድን እና በበሽር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የሚገኙ ሁለት የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል።
የአክቲቪስት ቡድኑ በሆስፒታሉ ግቢ በነጭ አንሶላ የተጠቀለሉ አስከሬኖችን የሚያሳይ ቪዲዮ ለቋል።
ለዚህ ጥቃት ተጠያቂው የትኛው ቡድን እንደሆነ ማረጋገጥ አልተቻለም።
በሱዳን አንድ ወቅት አጋር በነበሩት የሱዳን ጦር መሪ በጀነራል አልቡርሃን እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይልን በሚመሩት ጀነራል ሀምዳን መሀመድ ደጋሎ ወይም ሄሜቲ መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ነው።
ግጭቱን በዲፕሎሚሲያዊ መንገድ ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶች እስካሁን አልተሳኩም።