የሱዳን ተፋላሚዎች የ24 ሰዓት የተኩስ አቁም አወጁ
ሁለቱ ወገኖች በካርቱም የተካሄደውን ከባድ ውጊያ ተከትሎ ለአንድ ቀን የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት አደረጉ
ግጭቱ በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ከቅዳሜ ጀምሮ ቀጥሏል
ከቅዳሜ ጀምሮ ሲዋጉ የነበሩት የሱዳን የጦር አበጋዞች ከአሜሪካ ግፊት በኋላ ለ24 ሰዓታት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች ከማክሰኞ ምሽት ጀምሮ ለአንድ ቀን የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን
በካርቱም በተካሄደው ከባድ ጦርነት በዋሽንግተን የዲፕሎማቲክ ኮንቮይ ጥቃት መድረሱን ተከትሎ የሱዳንን ኃይሎች አስጠንቅቀዋል።
የሱዳን ገዥ ወታደራዊ ምክር ቤት አባል ጄኔራል ሻምስ ኤል ዲን ካባሺ በአል አረቢያ ቴሌቪዥን ቀርበው የተኩስ አቁም ስምምነቱ 12 ሰዓት ላይ ይጀምራል ብለዋል።
ስምምነት ከ24 ሰዓት በላይ አይራዘምም ሲሉም ተናግረዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
አንቶኒ ብሊንከን የጦሩ እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አዛዦችን በተናጠል አነጋግረዋል ተብሏል።
በስልጣን ሽኩቻው በመላ ሀገሪቱ ቢያንስ 185 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፤ ሱዳንን ወደ ሲቪል አገዛዝ ለመቀየር የተያዘውን እቅድም ቀልብሷል።
ግጭቱ በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ከቅዳሜ ጀምሮ ቀጥሏል።
የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ማህበራት ፌዴሬሽን በመዲናዋ ዙሪያ የሰብዓዊ አገልግሎት መስጠት ፈጽሞ የማይቻል ነገር ነው ብሏል።
የሀገሪቱ የጤና ስርዓት የመፍረስ አደጋ ላይ መሆኑንም አስጠንቅቋል።