ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በጥሩ ሁኔታ የተያዙ "የጦር እስረኞችን" ብቻ በእጁ እንዳሉ ተናግሯል
የሱዳን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በመዲናዋ ከአምስት ሽህ በላይ ሰዎችን ኢ-ሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ ማሰሩን ተናግረዋል።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የሀገሪቱን ዋና ከተማን በአመዛኙ በመቆጣጠር ከሱዳን ጦር ጋር ለሦስት ወራት ሲዋጋ ቆይቷል።
ነዋሪዎቹ ፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ቤት እየዘረፈ ነው ሲሉም መክሰሳቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በቀረበብተወ ውንጀላ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ተጠይቆ ሪፖርቶቹ የተሳሳቱ መሆናቸውን ገልጿል።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ"የጦር እስረኞችን" ብቻ በቁጥጥር ስር እንዳዋለ እና በጥሩ ሁኔታ እንደተያዙም ተናግሯል።
"እነዚህ ድርጅቶች በጦሩ የአየር እና የመድፍ ድብደባ፣ እስራት እና ሰላማዊ ዜጎችን ማስታጠቅን ጨምሮ በሰራዊቱ ላይ የሚፈጸመውን ጥሰት ችላ ብለዋል" ሲል የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ተወካይ በበኩላቸው ከሰዋል።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በካርቱም ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ከታሰሩት መካከል ተዋጊዎች እንደሚገኙበት ገልጸዋል።
ነገር ግን 3 ሽህ 500 ንጹኃን ዜጎች ለአደጋ የተጋለጡ ሴቶች እና የውጭ ዜጎችን መሆናቸውን ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት ድርጅቶቹ ተናግረዋል።
ቡድኑ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት "ከሰብዓዊ ክብር የራቁ ሁኔታዎችን" የሚያሳይ ሰነድ እንደሚያቀርብ ገልጿል።
የተመድ የሰብዓዊ መብት ቢሮ ሀሙስ ዕለት በዳርፉር ቢያንስ 87 ሰዎች በጅምላ መቃብር መገኘታቸውን ገልጾ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን እና ተባባሪ ሚሊሻዎችን ከሷል።
ሆኖም ክሱን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን አልተቀበለውም