ሚኒስቴሩ ሱዳን ኢጋድ ልትወጣ እንደምትችልም አስጠንቅቋል
የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "የውጭ ኃይሎችን" ወደ ሱዳን የመላክን ጥሪ እንደማይቀበለው አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ሱዳን ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት(ኢጋድ) ልትወጣ እንደምትችልም አስጠንቅቋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ የኢጋድን የውጭ ኃይሎችን ወደ ሀገሪቱ የመላክ እቅድ እንደማይቀበለው እና ሱዳንም ከኢጋድም ልትወጣ እንደምትችል አስጠንቅቋል።
ሚኒስቴሩ የውጭ ኃይሎች እንደወራሪ ይታያሉ ብሏል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን መግለጫ ያወጣው ኢጋድ በትናንትናው እለት በሱዳን ጉዳይ በአዲስ አበባ መምከሩን ተከትሎ ነው።
ሚኒስቴሩ እንደገጸው የሱዳን ልኡካን ቡድን በአዲስ አበባ መገኘት፣ ሱዳን ለሰላማዊ መፍትሄ ያላትን ጽኑ ፍላጎት የሚያሳይ ነው ብሏል።
ኢጋድ በአዲስ አበባ ባደረገው ስብሰባ ሁለቱንም የሱዳን ተፋላሚዎቹ እንዲገኙ መጋበዙን እና እነሱም ለመሳተፍ አረጋግጠው ነበር ብሏል።
ነገርግን የሱዳን ጦር በንግግሩ ላይ አለመገኘቱን እና ይህም እንዳሳዘነው ኢጋድ ገልጿል።
ኢጋድ በሱዳን ንጹሃን ሰዎችን ከጥቃት ለመከላከል ሰላም አስከባሪ ኃይል በመላክ ሀሳብ ላይም መምከሩን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።