ሱዳን የአፍሪካ ህብረት በግድቡ ዙሪያ ያለውን የኢትዮጵያ፤ግብጽና ሱዳን አለመግባባት መፍታት እንደማይችል ገለጸች
የአፍሪካ ህብረት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ዙሪያ ያጋጠመውን አለመግባባት “በራሱ መፍታት አይችለም” በማለት ሱዳን ቅሬታዋን አቅርባለች፡፡
የሱዳን ውሃ ሚኒስትር ያሲር አባስ እንደተናገሩት ህብረቱ ከፈረንጆቹ ጁላይ 2020 ጀምሮ ሲያደራድር ቢቆይም ተጨባጭ መፍትሄ አልመጣም ብለዋል፡፡ የህብረቱ ሊቀመንበር ፍሌክሲ ትሽኬዲ በሱዳን ተገኝተው መምከራቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ በምክክሩ አዲስ ነገር አለመገኘቱን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በግድቡ ዙሪያ የሚያደርጉትን የሶስትዮች ድርድር በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር እየተካሄደ ይገኛል፤ኢትዮጵያም ይህን ሂደቱን ትደግፋለች፡፡
ሚኒስትር ያሲር አባስ ኢትዮጵያ እየሄደችበት ያለውን መንገድ በመቃውም ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የጸጥታው ም/ቤት ቅሬታ ማቅረቡን ገልጿል፡፡ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ 2ኛ ዙር የግድቡን ውሃ ሙሌት ለማካሄድ መወሰኗ ትክክል አይደም ሲሉ ተቃውመዋል፡፡
ሚኒስትሩ እንተናገሩት ግድቡን በሚመለከት ሱዳን አሁም በፖለቲካውም ሆነ በህግ አግባብ ለመሄድ መወሰኗን ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ የአረብ ሊግ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በነገው እለት በኳታር እንደሚሰበሰቡና በህዳሴው ግድብ ላይ መክረው ጠንኳራ መግለጫ ያወጣሉ ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተደጋጋሚ እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ የግድቡን የውሃ ሙሌት በእቅዷ መሰረት እንደምትሞላና፤ ከመሙላት የሚያደናቅፋትን በማንኛውንም አይነት ወደኋላ እንደማትል ገልጻለች፡፡
የግድቡ የሶስትዮሽ ድርድር በአፍሪካ ህብረት አዳራዳሪነትና በአሜሪካና በአውሮፓ ህብረት ታዛቢነት ድርድር ለማካሄድ ተስማምተው፤ድርድር ሲያካሂዱ ቆይተዋል፡፡