የሱዳን ጦር መፈንቅለ መንግስቱን ለመቃወም በወጡ መምህራን ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኮሰ
ሰልፉን የጠራው የሱዳን ምሁራን ማህበር ፖሊሶች ህግ እንዲያከብሩ ጠይቋል
የሱዳን ጦር እስካሁን 14 ሰላማዊ ሰልፈኞችን ተኩሶ መግደሉ ተነግሯል
የሱዳን ጦር በሀገሪቱ የተፈፀመውን መፈንቅለ መንግስት ለመቃወም በወጡ መምህራን ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኮሰ።
በሱዳን ከ15 ቀናት በፊት በአገሪቱ ጦር በተመራው መፈንቅለ መንግስት የሲቪል አስተዳድሩ መፍረሱ የታወሳል።
ይህ የሲቪል አስተዳድር ከሁለት ዓመት በፊት በህዝብ ጥያቄ ነበር የወቅቱን ፕሬዘዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽርን በማስወገድ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ፖለቲካ ፓርቲዎች ተዋቅሮ መንግስት ሆኖ ነበር።
ይሁንና በዚህ ሲቪል አስተዳድር ላይ ሱዳን ጦር ዋና አዛዥ ጀነራል አልቡርሃን የተመራ መፈንቅለ መንግስት ከሁለት ሳምንት በፊት መፈጸሙ እና አመራሮቹም ወደ እስር ቤት ተወስደዋል።
ድርጊቱን በመቃወም ሱዳናዊያን በየጊዜው ወደ አደባባዮች በመውጣት የሲቪል አስተዳድሩ ወደ ቀድሞ ቦታው እንዲመለስ በመጠየቅ ላይ ናቸው።
ሰልፉን የተለያዩ የሱዳን የህብረተሰብ ክፍሎች ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ሲሆኑ በዛሬው ዕለት በሱዳን ምሁራን ማህበር ስር አንዱ የሆነው መምህራን ማህበር ሰላማዊ ሰልፍ ለማድርገ ወደ አደባባይ ወጥተዋል።
ይሁንና የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ በሱዳን የተለያዩ ከተሞች እንደተጀመረ የሱዳን ጦር እና ፖሊስ አስለቃሽ ጭሶችን ወደ ሰለፈኞቹ መተኮሱ ተገለጿል።
የሱዳን ምሁራን ማህበር የጸጥታ አካላት ሰላዊ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሃላፊነታችሁን ተወጡ ሲል ጥሪውን አቅርቧል።
በሱዳን መፈንቅለ መንግስት ከተፈጸመ በኃላ አሜሪካንን ጨምሮ አውሮፓ ህብረት እና ሌሎች ዓለም አቀፉ ተቋማት የሱዳን ጦር ስልጣኑን ለሲቪል አስተዳድሩ እንዲመልስ በማግባባት ላይ ናቸው።
የሱዳን ጦር እስካሁን ለሰላማዊ ሰልፍ ወደ አደባባይ ከወጡ ሰዎች መካከል 14 ሰዎችን ተኩሶ የገደለ ሲሆን በርካቶችን አቁስሏል።