ፖለቲካ
ሱዳን ከተመድ ተወካይ ጋር እንደማትተባበር አስታወቀች
የሱዳን መንግስት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ልዩ ተወካይ ጋር እንደማይተባበር አስታውቋል
የሱዳን ጦር ዋና አዛዥ አል ቡርሃን ቀደም ሲል በቴርትዝ ላይ ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል
የሱዳን መንግስት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ልዩ ተወካይ ጋር እንደማይተባበር አስታውቋል።
የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሱዳን መንግስት ከተመድ ዋና ጸኃፊ ተወካይ ከሆኑት ቮልከር ፔርትዝ ጋር ከዛሬ ጀምሮ እንደማይተባበር ገልጿል።
የሱዳን ጦር ዋና አዛዥ አል ቡርሃን ቀደም ሲል በቴርትዝ ላይ ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል።
የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች በአሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ ግፊት አማካኝነት በጂዳ ተኩስ አቁም እንዲደርሱ የተደረገው ጥረት አልተሳካም።
ተፋላሚ ኃይሎቹ ካርቱምን ጨምሮ በትላልቅ ከተሞች የሚያደርጉት ጦርነት ቀጥሏል።
አሜሪካ በጂዳ ካሉት የሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች ጋር በተለይም የሰብአዊ አገልግሎት አቅርቦት ማመቻቸትን በሚመለከት እየተነጋገረች መሆኗን ገልጻ ነበር።
ከዚህ በተጨማሪም አሜሪካ በሱዳን ያለውን ጦርነት የማባባስ ሚና አላቸው ያለቻቸውን ሁለቱንም ኃይሎች በሚደግፉ ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጥላለች።
ይህ ጦርነት ሱዳንን 30 አመታት በላይ የገዙት ፕሬዝደንት አልበሽር በህዝባዊ አመጽ ከስልጣን መውረዳቸውን ተከትሎ ሊቋቋም የነበረው የሲቪል አስተዳደር አምክኗል።