አገሪቱ ባሳለፍነው ሳምንት ዜጎቿ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ አሳስባ ነበር
ሱዳን ዜጎቿ በአስቸኳይ ከኢትዮጵያ እንዲወጡ በድጋሚ አሳሰበች፡፡
በአዲስ አበባ የሚገኘው የሱዳን ኢምባሲ ባወጣው ማሳሰቢያ ሱዳናዊያን በአስቸኳይ ኢትዮጵያን ለቃችሁ ውጡ ብሏል፡፡
ሱዳናዊያን የንግድ አውሮፕላኖችን በመጠቀም ወደ አገራቸው እንዲጓዙ ያሳሰበው የሱዳን ኢምባሲ ይሄንን ለሚያደርጉ ዜጎች ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጿል፡፡
ሱዳን ከሁለት ሳምንት በፊት አስገዳጅ ሁኔታ እስካልገጠማቸው ድረስ ዜጎቿ በፈቃደኝነት ኢትዮጵያን ለቀው ለመውጣት እንዲዘጋጁ አሳስባ ነበር በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ባወጣችው መግለጫ፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ዜጎቿ ከአዲስ አበባ ውጭ እንዳይጓዙ ከማስጠንቀቁ በተጨማሪ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የሚገኙ ሱዳናውያንን ተጠንቀቁ ስትልም ነበር ያሳሰበችው፡፡
“በምትንቀሳቀሱበትም ሆነ በየትኛውም አጋጣሚ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዛችሁን እንዳትረሱ” ሲልም ነው “ከመሰባሰቦች ራቁ ከአዲስ አበባ ውጭ ብዙ አትጓዙ”ሲል ያሳሰበው ኤምባሲው ያስታወቀው፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን የተደረገውን የፖለቲካ ስምምነት አደነቀ
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን በማስታወስም አስገዳጅ ሁኔታዎች ካልገጠሟቸው በስተቀር ሱዳናውያኑ ኢትዮጵያን ለቆ ለመውጣት የሚያስችላቸውን አስፈላጊውን የበረራ ዝግጅት በፈቃደኝነት እንዲያደርጉም አሳስቧል፡፡
ኤምባሲው በማሳሰቢያው ላይ ለውጦችን ሊያደርግ እንደሚችል እና በኢትዮጵያ የሱዳን ዜጎችን ደህንነትና ደህንነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ አስታውቋል።
በቅርቡ መፈንቅለ መንግስት ያስተናገደቸው ሱዳን ራሷ የተረጋጋ ፖለቲካዊ ሁናቴ ላይ እንደማትገኝ ነው የሚነገረው፡፡