ተመድን ጨምሮ በርካታ ሀገራት የሱዳን ፖለቲከኞች ወደ ስምምነት እንዲመጡ ሲወተውቱ እንደነበር ይታወሳል
የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን የሲቪል እና ወታደራዊ አካላት መካከል የተደረገውን የስልጣን ክፍፍል ማእከል ያደረገ የፖለቲካ ስምምነት አደነቀ።
አብደላ ሃምዶክ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው እንዲመለሱ እና ካቢኔያቸውን እንዲያዋቅሩ መደረጉ የሚያስመሰግን ነው”ም ነው ያለው የኢትዮጵያ መንግስት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስርያ ቤት በኩል ባወጣው መግለጫው።
የሽግግሩ ጊዜ ሁሉም ተቋማት ወደነበሩበት መመለሳቸው እና ህገ መንግስታዊ አዋጁ ህጋዊ የአስተዳደር ሰነድ እንዲሆን ከስምምነት መደረሱ የሚበረታታ ነውም ብሏል።
በሌነታል ጀነራል አል-ቡርሃን እና በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ መካከል የተደረገው አዲሱ የስልጣን ክፍፍል ስምምነት በቀጠናው በአጠቃላይ በሱዳን ደግሞ በተለይ፤ ሰላምና መረጋጋት ያመጣል የሚል ተስፋ እንዳለውም የኢትዮጵያ መንግስት ገልጸዋል።
በሱዳን በሃገሪቱ ጦር ዋና አዛዥ ጀነራል አብዱል ፋታህ አልቡርሃን የሚመራ ጦር ዩዳን ሲቪል አስተዳሩ ላይ መፈንቅለ መንግስት በመፈፀም አዲስ ወታደራዊ መንግስት መመስረቱ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎም በወታደሩ ተግባር የተበሳጩ ሱዳናውያን በካርቱም እና በሌሎችም የሀገሪቱ ጎዳናዎች ላይ በመውጣት ቁጣቸውን ሲገልጹ ነበረ ሲሆን፤ በተቃውሞ ሰልፎቹ ላይ በሱዳን ጦር የተገደሉ ሰላማዊ ሰልፈኞች ቁጥር 40 ደርሷል።
ተመድ፣ አፍሪካ ህብረት እና ኢጋድን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ወታደራዊ አመራሩ ስልጣኑን ለሲቪል አስተዳድር እንዲመልስ ድርድር እንዲጀመር ሲወተውቱ መቆየታቸውም አይዘነጋም።