ተፋላሚዎቹ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ተቀስቅሶ ወደ ሌሎች አካባቢ የተስፋፋውን ጦርነት በመጀመር አንዳቸው ሌላኛቸውን ሲከሱ ተደምጠዋል
የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች በተመድ ስብሰባ እርስ በእርሱ የሚቃረን መግለጫ ሰጥተዋል።
የሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች መሪዎች አንጀኛው ከመድረክ እና ሌላኛው ደግሞ ካልታወቀ ቦታ በመሆን በስብሰባው ላይ መግለጫ መስጠታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሱዳን ጦር መሪ አል ቡርሃን አለምአቀፉ ማህበረሰብ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎችን በሽብርተኝነት እንዲፈርጅ እና ከሱዳን ድንበር ውጭ ላሉት አጋሮቹ አጸፋ ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መሪ መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሚቲ ባሰሙት የቪዲዮ መልእክት ለተኩስ አቁም እና ለአካታች የፖለቲካ ንግግር ዝግጁ መሆናቸውን ተናግዋል።
ተፋላሚዎቹ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ተቀስቅሶ ወደ ሌሎች አካባቢ የተስፋፋውን ጦርነት በመጀመር አንዳቸው ሌላኛቸውን ሲከሱ ተደምጠዋል።
ሄሜቲ አል ቡርሃን ከመናገራቸው በፊት ባሰሙት የቪዲዮ የሱዳን ብሄራዊ ሰንደቅ አላማ ከኋላቸው በማድረግ መግለጫቸውን አንብበዋል።
ለሶስት አስርት አመታት የመሩት አል በሽር በህዝባዊ አመጽ ከወደቁ በኋላ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ወደ ብሄራዊ ጦሩ ለመቀላቀል የታያዘው እቅድ ለጦርነቱ መጀመር ምክንያት ሆኗል።
ጦርነቱ ምክንያቱ አምስት ሚሊዮን ሰዎችን አፈናቅሏል።