ፖለቲካ
በሱዳን ጦር ስር በቆየችው ፖርት ሱዳን ውስጥ ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ
ኃላፊው እንደገለጹት የጥምረቱ ሚሊሻ እና ጦሩ ተኩስ ቢለዋወጡም የደረሰ ጉዳት የለም ብለዋል
ድራር በስም ያልጠቀሷቸውን አካላት የሬድ ሲ ግዛትን ሀብት በማባከን እና በመበዝበዝ ከሰዋል
የምስራቅ ሱዳን ፖርቲዎች እና ንቅናቄዎች ኃላፊ ሼይባ ድራር አል ሁራ ለተሰኘው ቲቪ በሰጡት ቃለ ምልልስ የሱዳን ጦር በፖርት ሱዳን በዲም መንደር ውስጥ የሚገኘውን የጥምረቱን ዋና መቀመጫ ማጥቃቱን ገልጸዋል።
ኃላፊው እንደገለጹት የጥምረቱ ሚሊሻ እና ጦሩ ተኩስ ቢለዋወጡም የደረሰ ጉዳት የለም ብለዋል።
ግጭቱ የተከሰተው በጥምረቱ ዋና መቀመጫ ፊትለፊት የነበሩት የጥምረቱ ሚሊሻዎች ህጋዊ ፈቃድ ያልያዙ ከፖርት ሱዳን እቃ ጭነው ሲመጡ የነበሩትን መኪናዎች በሚፈትሹበት ወቅት ነው።
ድራር በስም ያልጠቀሷቸውን አካላት የሬድ ሲ ግዛትን ሀብት በማባከን እና በመበዝበዝ ከሰዋል። ድራር እንደገለጹት በችግሩ ዙሪያ ውይይት እየተካሄደም ነው።
ይህ የሆነው በጀነራል አልቡርሃን በሚመራው የሱዳን ጦር እና በጀነራል መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሚቲ መካከል ባለፈው ሚያዝያ ወር የተጀመረው ጦርነት በቀጠለበት ወቅት ነው።
አምስት ወራትን ያስቆጠረው የሱዳን ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲገደሉ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ሀገራቸውን ለቀው እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል።
በሱዳን በብዙ ቦታዎች ከፍተኛ የሆነ የምግብ፣ የመድሃኒት እና የነዳጅ እጥረት ተከስቷል።