የስዊድን ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት ማግደሊና አንደርሰን ፓርቲያቸው በምርጫ መሸነፉን ተከትሎ ስልጣን ለማስረከብ ተገደዋል
ኡልፍ ክሪስቴርሰን የስዊድን ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ተመረጡ
አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር በስደተኞች ላይ አሉታዊ አመለካከት እንዳላቸው ተገልጿል
የስዊድን ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት ማግደሊና አንደርሰን ፓርቲያቸው በምርጫ መሸነፉን ተከትሎ ስልጣን ለማስረከብ ተገደዋል
ኡልፍ ክሪስቴርሰን የስዊድን ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ተመረጡ።
ለረጅም ዓመታት በሶሻል ዲሞክራሲ ስትተዳደር የነበረችው ስዊድን ከ70 ዓመት በኋላ በቀኝ ዘመም ወይም ወግ አጥባቂ ፓርቲ እንደምትመራ ተገልጿል።
የሞደሬት ፓርቲ መሪ የሆኑት ኡልፍ ክሪስትርሰን የስዊድን ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው እንደተመረጡ ሮይተርስ ዘግቧል።
በስዊድን ከአንድ ወር በፊት በተካሄደ የምክር ቤት ምርጫ በስልጣን ላይ ያለው የሶሻል ዲሞክራቲ ፓርቲ በቀኝ ዘመም ፓርቲዎች አብላጫ ተወስዶበታል።
ይሄንን ተከትሎም ወግ አጥባቂ የስዊድን ፓርቲዎች በአብላጫ ድምጽ የሀገሪቱን ህግ አውጪ ምክር ቤት መቀመጫዎችን ይዘዋል።
እነዚህ አሸናፊ ፓርቲዎች አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር የመረጡ ሲሆን የሞደሬት ፓርቲ መሪ ኡልፍ ክርስተርሰንን 176 ለ173 በሆነ ድምጽ መርጠዋል።
የ58 ዓመቱ ክርስተርሰን በጸረ ስድተኞች አቋማቸው የሚታወቁ ሲሆን ስደተኞች በስዊድን ለሚከሰቱ የሽብር ድርጊቶች ዋነኛ ተሳታፊዎች እንደሆኑ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ተናግረዋል ።
በዚህ ምክንያትም የስዊድን ስደተኞች ፖሊሲን እንደሚያጠብቁ የሚጠበቅ ሲሆን የጦር መሳሪያ ህጎችንም ጥብቅ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ይጠበቃል።
አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ክርስተርሰን ፓርቲያቸው በምርጫው የተሸነፈባቸው እና ከወቅቱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ማግደሊና አንደርሰን ስልጣን በቅርቡ ይረከባሉ ተብሏል።
ሩሲያ ለልዩ ዘመቻ በሚል ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን መላኳን እና ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ ስዊድን የኔቶ አባል ለመሆን ጥያቄ አቅርባለች።
አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ኡልፍ ክርስተርሰን ሀገራቸው የኔቶ አባል ለመሆን ያቀረበችውን ጥያቄ እንሰሚያስፈጽሙም ይጠበቃል።