የሱዳን ሲቪሊያን ቡድኖች ወታደሩ ከፖለቲካ ሙሉበሙሉ እና በፍጥነት ከፖለቲካ እንዲወጣ ይፈልጋሉ
የሱዳን ወታደራዊ መሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር እና ፕሬዝደንት ከሲቪሊያ ፖለቲከኞች እንዲሾሙ በመርህ ደረጃ ተስማምተዋል፡፡
ጄነራል ሀምዳን ዳጋሎ ከሱዳን ሉአላዊ የሽግግር መሪ ከጄነራል አልቡርሃን ጋር ከስተሰተሰቡ በኋላ ባወጡት መግለጫ ሲቪሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሾም መስማማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ጄነራሎቹ የሲቪል መንግስት ከተቋቋመ በኋላ ወታደሩ ከፖለቲካ ተሳትፎ እንደሚወጣና በህገመንግስት ወደተቀመጠለት ኃላፊነት ትኩረት እንደሚያደርግ በመግጫው አስታውቀዋል፡፡
የሱዳን ወደታደር በላፈው ጥቅምት ወር መፈንቅለ መንግስት በማድረግ ከሲቪሊያን ጋር የነበረው የስልጣን መጋራት እንዲያበቃ እና ሀገረቱም ወደ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋት ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል፡፡
በአፍሪካ ህብረት፤ በተመድ እና በውጭ ኃይሎች የነበረው የማደራደር ጥረት ፍሬ አላፈራም፡፡ የሱዳን ሲቪሊያን ቡድኖች ወታደሩ ከፖለቲካ ሙሉበሙሉ እና በፍጥነት ከፖለቲካ እንዲወጣ ይፈልጋሉ፡፡
ቡርሃን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ የአሜሪካን፣የብሪታኒያን፣ የሳኡዲ አረቢያን እና የአረብ ኢምሬትስን አምባሳደሮች አግኝተው አነጋግረዋል፡፡
በሱዳን ወታደራዊ አገዛዞችን የሚቃወሙ ሰልፎች በተለያየ ጊዜ ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡