አምባሳደር ይበልጣል በኢትዮጵያ አየር ክልል ከተመታው አውሮፕላን ጋር በተያያዘ የየትኛውንም ሀገር ስም አልጠቀሱም- በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ
ሱዳን ተመቶ ወድቋል በተባለው የጦር አውሮፕላን ጉዳይ የኢትዮጵን አምባሳደር ለማብራሪያ ጠርታለች
በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ያለአግባብ ስሜ ተነስቷል ላለችው ሱዳን ምላሽ ሰጥቷል
አምባሳደር ይበልጣል በኢትዮጵያ አየር ክልል ተመትቶ ከወደቀው ጦር አውሮፕላን ጋር በተያያዘ የየትኛውንም ሀገር ስም አለመጥቀሳቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገለፀ።
በሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር ይበልጣል እምሮ ከሰሞኑ በካርቱም ለመገናኛ ብዙሃን ከሰጡት መግለጫ ጋር ተያየዞ ለተፈጠረው ብዥታ ማብራሪያ የሚሆን መግለጫ አውጥቷል።
አምባሳደሩ በሰጡት መግለጫ ላይ በርካታ ጉዳዮች መነሳታቸውን ያስታወቀው ኤምባሲው፤ ከሰሞኑ ለህወሓት የጦር መሳሪያ ሊያቀርብ ሲል በኢትዮጵያ አየር ኃይል ተመትቶ ስለወደቀው የጦር አውሮፕላን ጉዳይ ከጋዜጠኞች ጥያቄ እንደተነሳላቸውም አስታውቋል።
አምባሳደሩ በሰጡት ምለሽ “አውሮፕላኑ ተመትቶ መውደቁ እውነት መሆኑን አረጋግጠዋል፤ ነገር ግን የየትኛውንመ ሀገር ስም ከአውሮፕላኑ ጋር ተያይ አልጠቀሱም” ብሏል ኤምባሲው በመግለጫው።
ሆኖም ግን አንድ አንድ የመገናኛ ብዙሃን በአምባሳደሩ የተናገሩትን ከአውድ ውጪ በተዛባ መልኩ መጠቀማቸውን እና ይህም እንዳሳዘነው ኤምባሲው አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች ያለው ኤምባሲው፤ ሁለቱ እህትማማች ሀገሮች ግንነኙነታቸውን በየደረጃው ለማጠናከር ተቀራርበው እየሰሩ ነው ብሏል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ባሳለፍነው ሳምንት በሱዳን በኩል የኢትዮጵያን አየር ክልል በመጣስ በህወሓት ቁጥጥር ስራ ወዳሉ የትግራይ ክልል እየበረረ የነበር አውሮፕላን መመታቱን ተናግረው ነበር።
በካርቱም የኢትዮጵያ አምባሳደርን ይበልጣል አዕምሮ ከሰሞኑ በካርቱም በሰጡት መግለጫ ላይ አውሮፕላኖ ተመትቶ ስለመውደቁ የወጣው መረጃ ትክክል መሆኑን ብዙሀን መገናኛዎች አረጋግጠዋል ተብሏል።
ይሄንን ተከትሎም የሱዳን ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮን ለተጨማሪ ማብራሪያ መጥራቱን ቡካርቱም ያለው የአል ዐይን ዘጋቢ አረጋግጧል።
በሱዳን ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ፋድል አብዱላሂ በካርቱም የኢትዮጵያ አምባሳደር የሱዳንን ስም አጥፍተዋል ሲሉ ከሰዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም "አምባሳደር ይበልጣል ያልተገባ ነገር ለሱዳን ብዙሀን መገናኛዎች ተናግረዋል፣ ንግግራቸውም የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያበላሻል" ብለዋል።
በተለይም ሁለቱ ሀገራት ግንኙነታቸውን ለማስተካከል እየጣሩ ባለበት ባሁኑ ወቅት አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ የተናገሩት ንግግር የሱዳንን ብሄራዊ ህግ የሚጥስ ነውም ብለዋል ዳይሬክተሩ።