በሱዳን በጄነራል አል ቡርሃን እና በጀነራል ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ መካከል የተጀመረው ጦርነት ሶስት ሳምንታትን አስቆጥሯል
ሱዳናውያን የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች በጂዳ እያካሄዱት ባለው ድርድር ቀውሱ እልባት ያገኛል የሚል ተስፋ ሰንቀዋል።
በጦርነቱ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ሀገራቸየውን ለቀው ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰደዋል።
በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል ባለፈው ቅዳሜ በሳኡዲ አረቢያ ጂዳ የተጀመረው ድርድር መሻሻል አላሳየም ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ተፋላሚዎቹ በጂዳ ንግግራቸው የሰብአዊ ተኩስ አቁም ለማክበር መነጋገራቸው ተገለጿል
በሱዳን ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የተደረሱ በርካታ የተኩስ ማቆም ስምምነቶች ተጥሰዋል
በትናንትናው እለት የሱዳን ጦሪ መሪ የሆኑት ጀነራል አልቡርሃን ጦሩ ሰላማዊ መፍትሄ እንደሚፈልግ እና ዘላቂ መፍትሄ የሚኖረው ግን በካርቱም ዘላቂ ተኩስ አቁም ከተደረሰ በኋላ ነው ብለዋል።
ነገርግን በሱዳን የአየር ድብደባ ድምጽ ሲያስተጋባ ነበር፤ በካርቱም ከተማ የተለያዩ አካባቢዎችም ግጭት መስተዋላቸው ተገልጿል።
በሱዳን በጄነራል አል ቡርሃን እና በጀነራል ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ መካከል የተጀመረው ጦርነት ሶስት ሳምንታትን አስቆጥሯልበሱዳን በጄነራል አል ቡርሃን እና በጀነራል ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ መካከል የተጀመረው ጦርነት ሶስት ሳምንታትን አስቆጥሯል