ሱዳናውያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክና ወታደራዊ መሪው ያደረጉትን ሰምምነት በመቃወም ሰልፍ ወጡ
የነጻነትና የለውጥ ሃይል ፓርቲ መሪዎች ታስረዋል ተብሏል
ሰልፈኞቹ “ትብብር የለም፤ስምምነት የለም፤ ቅቡልነት የለም” የሚል ይዘት ያላቸውን መፈክሮች አሰምተዋል
በሱዳን ወታደራዊ መሪና በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ መካከል የተደረገውን ፖለቲካዊ ስምምነት በመቃወም በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን በካርቱም አደባባይ ወጥተዋል፡፡
ሰልፈኞቹ “ትብብር የለም፤ስምምነት የለም፤ ቅቡልነት የለም” የሚል ይዘት ያላቸውን መፈክሮችን አሰምተዋል፤ የሲቪሊያን አስተዳደር እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
የነጻነትና የለውጥ ሃይል ፓርቲ ደጋፊዎች፣ የሱዳን ወታደራዊ መሪ አብደል ፈታ አልቡርሃን የሉአላዊነትንና ሚኒስትሮች ም/ቤት ካፈረሱና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጁ በኋላ ተቃሟቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡
የዛሬው የሱዳን ሰልፍ የሪዝስታንስ ኮሚቴ ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የተካሄደ ሲሆን አላማውም ገዥው ቡድን ፍላጎታቸውን እንዲሰማ ማድረግ ነው፡፡ አል ዐይን ኒውስ ሰልፈኞቹ በካርቱም ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ባህር ከተማ፤ ስቴሽን ሰባት በሚባለው በካርቱም ደቡባዊ ክፍልና ሲክስቲ ስትሪት በተባሉ አካባቢዎች ሰልፈኞች አብዮቱ ፍጻሜውን እንዲያገኝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ቀደም እንዳሉት ከወታደራዊ መሪው አልቡርሃን ጋር ያደረጉት ስምምነት አላማው ደምመፋሰስን ለማስቆም ነው ብለዋል፡፡ እንደ ሱዳኑ የዶክተሮች ማእከላዊ ኮሚቴ ከሆነ አልቡርሃን አስቸኳይ ጊዜ ጀምሮ በተካሄዱ ሰልፎች 42 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ሰልፎቹን ተከትሎም በአብዛኛው የነጻነትና የለውጥ ሃይል ፓርቲ መሪዎች መታሰራቸው ተዘግቧል፡፡