የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ተኩስ ለማቆም ቢስማሙም የተኩስ ድምጽ እየተሰማ ነው
ሀገራት በሱዳን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዲኘሎማቶቻቸውን ለማውጣት በጥድፊያ ላይ ናቸው
በሱዳን የተቀሰቀሰው ግጭት ሀገሪቱ ወደ ዲሞክራሲያዊ የሲቪል መንግስት ለመሸጋገር የምታደርገውን ጥረት የናደ ነው ተብሏል
የሱዳን ተፋላሚዎች ከትናንት ጠዋት ጀምሮ ለ72 ሰአታት የሚቆ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ቢደርሱም፣በድጋሚ የተኩስ ድምጽ በመሰማት ላይ ነው።
የተመድ መልእክተኛ ተኩስ አቁም በከፊል ተግባራዊ መሆኑን እና ሁሉም አካላት እውነተኛ ንግግር ለማድረግ ዝግጅ መሆናቸውን የሚያሳይ ምልክት የለም ብለዋል።
በሱዳን ጦር እና በጀነራል ሀምዳን ደጋሎ በሚመራው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል የተደመረው ጦርነት አንድ ሳምንት ያለፈው ሲሆን በለያዩ ጊዜ የተደረጉ የተኩስ አቁም ስምምነቶች ተግባራዊ አልሆኑም።
የቅርቡ በአሜሪካ እና በሳኡዲ አረቢያ አደራዳሪነት የተደረሰው ተኩስ አቁም ሲጀመር ተግባራዊ የነበረ ቢሆንም ሙሉበሙሉ ተግባራዊ አልሆነም።
በድጋሚ የተኩስ ድምጾች እየተሰሙ መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የካርቱም እህት ከተማ በሆነችው ኦምዱርማን አመሻሽ ላይ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር ሮይተርስ በዘገባው ጠቅሷል።
የሱዳን ጦርም በሱዳን ሶስተኛ በሆነችው ባህሪ ከተማ ከሚገኘው የነዳጅ ማጣሪያ ታጣቂዎችን ለማባረር ድሮን ሲጠቀም ነበር ተብሏል።
የተመድ የሱዳን ልዩ ተወካይ ፐርተስ ሁለቱም ተፋላሚ ኃይሎች ለእውነተኛ ንግግር ዝግጁ አለመሆናቸውን እና ተኩስ አቁሙም በተወሰነ ቦታ ተግባራዊ መሆኑን ተናግረዋል።
ፐርተስ ይህ የተሳሳተ ስሌት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በሱዳን የተቀሰቀሰው ግጭት ሀገሪቱ ወደ ዲሞክራሲያዊ የሲቪል መንግስት ለመሸጋገር የምታደርገውን ጥረት የናደ ነው ተብሏል።
ሀገራት በሱዳን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዲኘሎማቶቻቸውን ለማውጣት በጥድፊያ ላይ ናቸው።