የሱዳን ጦር አሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ ተኩስ አቁሙ እንዲደረስ ማደራደራቸውን ገልጿል
የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ከዛሬ ጀምሮ ለ72 ሰአት የሚቆይ ተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሱዳን ለማስወጣት ጥድፊያ ላይ ናቸው።
- “የሱዳንን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ”- ጄነራል ዳጋሎ
- ጠ/ሚ ዐቢይ “በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ግጭት ለመቀስቀስ እየሰሩ ነው” ያሉ አካላትን አስጠነቀቁ
በሱዳን ጦር እና በጀነራል ደጋሎ በሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል መካከል የተፈጠረው ግጭት አንድ ሳምንት ያለፈው ሲሆን ጦርነቱ ድንገት በመከሰቱ የውጭ ዜጎች አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንዲወድቁ አድርጓቸዋል።
የሱዳን ጦር አሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ ተኩስ አቁሙ እንዲደረስ ማደራደራቸውን ገልጿል።
የስምምነቱን መደረስ የተናገሩት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ተኩስ አቁሙ እንዲደረስ ለማድረግ ለሁለት ቀን ብርቱ ውይይት ተካሂዷል ብለዋል።
ሁለቱ ተፋላሚዎች ተኩስ ለማቆም በተለያየ ጊዜ ቢስማሙም ተግባራዊ ሳያደርጉ ቆይተዋል።
በግጭቱ እስካሁን 427 ሰዎች ተገድለዋል።
ብሊንከን እንደገለጹት ተኩስ አቁም ስምምነቱ እንዲተገበር አሜሪካ ከአለም አቀፍና ከሱዳን ሲቪሊያን ቡድኖች ጋር ክትትል ታደርጋለች።
ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ባወጣው መግለጫ ለሰብአዊነት ሲል ስምምነቱን ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
የሱዳን ጦርም በተመሳሳይ ለተደረሰው ተኩስ አቁም እንደሚገዛ አስታውቋል።
የድርድሩ አካል የነበረው የሱዳን የሲቪል ሶሳይቲ ቡድን ስምምነቱን በበጎ ተቀብሎታል።
ከስምምነቱ ቀደም ብሎ በሱዳን ዋና ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ ከተሞች የአየር ድብደባ እና የመሬት ላይ ጦርነት ሲካሄድ እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል።
የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ቀይ ባህርን፣ የአፍሪካ ቀንድን እና የሳሃል ቀጠናን ባቀፈችው ሱዳን የተነሳው ግጭት አደገኛ ቀውስ የሚያስከትል ነው ብለዋል።
የተመድ የጸጥታው ምክርቤት በዛሬው እለት በሱዳን ጉዳይ ስብሰባ ጠርቷል።