የኮፕ 28ን ስኬት ለማረጋገጥ 'የነባር ህዝቦች' አስተዋጾ ወሳኝ ነው- ሱልጣን አል ጃበር
አረብ ኤምሬትስ ፍትኃዊ እና ግልጽነት ያለው የአየር ንብረት ጉባኤ ለማዘጋጀት ቃል ገብታለች
ኮፕ 28 ከዓለም ህዝብ አምስት በመቶ የሚሆኑትን ነባር የአገሬው ተወላጆችን ያካትታል ተብሏል
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የአየር ንብረት ለውጥ ልዩ መልዕክተኛ እና የኮፕ 28 ጉባኤ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃበር ለአየር ንብረት እርምጃዎች የነባር ህዝቦች ሚና አስፈላጊ መሆኑን አስምረዋል።
ፕሬዝዳንቱ በቦን የአየር ንብረት ስብሰባ ውስጥ ከነባር ህዝብ ተወላጆች ጋር ባደረጉት ስብሰባ በአየር ንብረት እንቅስቃሴ ውስጥ አስፈላጊነታቸው ላይ አጽንዖት ሰጥተዋል።
ኮፕ 28 ነባር የሚባሉ የአገሬው ተወላጆችን እንደሚያካትትም ጠቁመዋል።
- የአየር ንብረት ፋይናንስ ጉዳይን መፍታት በኮፕ28 ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው- ዶ/ር ሱልጣን አልጃበር
- በዱባይ በሚካሄደው ኮፕ28 ጉባኤ ኢትዮጵያ ምን ይዛ ትቅረብ?
አክለውም የአገሬው ተወላጆች አምስት በመቶ የሚሆነውን ህዝብ እንደሚወክሉ እና ከ80 በመቶ በላይ የዓለም ብዝሃ ህይወትን በመጠበቅ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ የኮፕ 28 ስኬትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ዶ/ር ሱልጣን አል ጃብር የቦን የአየር ንብረት ስብሰባዎች ትርጉም ያላቸው እና ተግባራዊ ውጤቶችን በመቅረጽ ረገድ ወሳኝ ናቸው ብለዋል።
የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ሴክሬታሪያት ባወጣው መግለጫ ዶ/ር ሱልጣን አል ጃብር ሁሉም አካላት በአጀንዳው መግባባት ላይ እንዲደርሱ የሚያስችል ፍትኃዊ፣ ሁሉን አቀፍ እና ግልጽነት ያለው ጉባኤ እንደሚያዘጋጁ እናረጋግጣለን ብለዋል።
ይህም የአየር ንብረት ፋይናንስን የበለጠ ተደራሽ ማድረግን፣ የማስተካከያ ፋይናንስን በእጥፍ ማሳደግ፣ የኪሳራ እና ጉዳት ፈንድ ማስጀመር ያካትታል።
በተጨማሪም በ2030 የዓለም ታዳሽ ኃይል አቅም በሦስት እጥፍ ማሳደግ እንዲሁም ወጣቶችን፣ ተፈጥሮን እና ጤናን ለአየር ንብረት እድገት ማዕከል ማድረግን ያጠቃልላል።
ዶ/ር ሱልጣን አል ጃብር አክለውም በሁሉም አቅጣጫዎች የላቀ እድገት እንዲመጣ ለሁሉም አካል ጥሪያችንን እናቀርባለን ብለዋል።
በያዝነው ሳምንት የተጀመረው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እስከ ሰኔ 15 በቦን ጀርመን ይካሄዳል።