ኪም ካርዳሺያንን ለመምሰል 1 ሚሊዮን ዶላር ያወጣችው ሴት
ብራዚሊያዊቷ ጀኒፈር ፓምፕሎና 30 የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ሕክምና አድርጋለች
እንስቷ ባደረገቻቸው የቀዶ ሕክምና ምክንያት መውለድ አለማችልን ጨምሮ የሰውነት አካል መዛባት አጋጥሟታል
ኪም ካርዳሺያንን ለመምሰል 1 ሚሊዮን ዶላር ያወጣችው ሴት
ብራዚሊያዊቷ ጀኒፈር ፓምፕሎና የዝነኛዋ አሜሪካዊት የፋሺን ሰው አድናቂ ናት፡፡
ከ17 ዓመቷ ጀምሮም ኪም ካርዳሺያንን ለመምሰል የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና ስታደርግ ቆይታለች፡፡
ይህች እንስት እስካሁን ለቀዶ ሕክምና ያወጣችው ወጪ አንድ ሚሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን በመጨረሻም ህይወቷን በስቃይ እንዲሞላ መሆኑን ለኒዮርክ ፖስት ተናግራለች፡፡
ከ1 ሚሊየን በአንዷ የሚፈጠር አስገራሚ ክስተት - በሁለት ማህጸን መጸነስ
እንደ ዘገባው ከሆነ ጀኒፈር ካርዳሺያንን ለመምሰል በፊቷ እና ዳሌዋ ላይ ያደረገቻቸው የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምናዎች ለተወሳሰበ የጤና ችግሮች ዳርጓታል፡፡
ለአብነትም በዳላዋ ላይ ያሰራችው የፕላስቲክ ቀዶ ህክምና ቦታውን በመልቀቅ ተፈጥሯዊ የመራቢያ የሰውነት ክፍሎቿን ቦታ አዛንፏል የተባለ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ልጅ መውለድ እንዳትችል አድርጓታል፡፡
እንዲሁም ለጀርባ እና ዳሌ ህመሞች መዳረጓን የምትናገረው ይህች ብራዚሊያዊት በህይወቷ ያተረፈችው ከባድ ስቃይ እና የገንዘብ ክስረት መሆኗንም ተናግራለች፡፡
ወጣቶች ራሳቸውን ብቻ እንዲመስሉ የምትመክረው ጀኒፈር በቀጣይ ከስቃይ ለመዳን የመጨረሻ የህክምና ሙከራ አደርጋለሁ ብላለች፡፡