በሻንግሻ ከተማ ባጋጠመው የህንጻ መደርመስ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል
አንዲት ቻይናዊት ከስድስት ቀናት በፊት ከተደረመሰ ባለ ስድስት ፎቅ ህንጻ ፍርስራሽ ስር በህይወት ተገኘች፡፡
ቻይናዊቷ ከስድስት ቀናት በኋላ በህይወት መገኘቷ እያነጋገረ ነው፡፡
በማዕከላዊ ቻይና ሁናን ግዛት ሻንግሻ ከተማ ባጋጠመው በዚህ ከፊል የህንጻ መደርመስ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
አስር ሰዎችን በህይወት ለመታደግ የተቻለም ሲሆን እስካሁን የደረሱበት ያልታወቀ ሰዎችም አሉ፡፡
ያለፉትን ስድስት ቀናት በፍርስራሹ ስር አሳልፋለች የተባለላት ቻይናት ግን ትናንት ሃሙስ ከ132 ሰዓታት ቆይታ በኋላ በህይወት ተገኝታ ከፍርስራሹ ስር ወጥታለች፡፡
ይህን ከአደጋው ሰለባዎች በህይወት የተገኘች 11ኛ ሴት ተብላለች፡፡
ሴትዮዋ ራሷን መቆጣጠር በምትችልበት ሁኔታ ላይ መሆኗን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ገልጸዋል፡፡
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቹ በአነፍናፊ ውሻዎች፣ በሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮን) እና በኤሌክትሮኒክስ ዘዴዎች በመታገዝ ሴትዮዋን ለመታደግ መቻላቸውን የሃገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡
ህንጻ መኖሪያን ጨምሮ የቢሮና ሌሎችንም ግልጋሎቶች ይሰጥ ነበረ፡፡ ሆኖም አደጋውን ተከትሎ የህንጻውን ባለቤት ጨምሮ አስር ሰዎች መያዛቸውም ተነግሯል፡፡