ሩሲያ ከቀድሞ የሶቪየት ህብረት አባል ሀገራት ጋር የነበራት የነዳጅ የግብይት መጠን በ25 በመቶ ቀንሷል
ቻይና ከሩሲያ የምትገዛውን የነዳጅ መጠን በ60 በመቶ አሳደገች፡፡
ሩሲያ ከጎረቤቷ ዩክሬን ጋር ጦርነት ከጀመረች ሁለት ወር ያለፋት ሲሆን እስካሁን ስድስት ሚሊዮን ገደማ ዩክሬናዊያን ሀገራቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡
በጦርነቱ ምክንያት አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሀገራትና ሌሎች አጋሮቿ በሩሲያ ላይ ከ6 ሺህ በላይ ማዕቀቦችን ጥለዋል፡፡
ማዕቀቡ በዋናነት ሀገራት የሩሲያ ነዳጅን እንዳይገዙ የሚያስገድድ ቢሆንም ቻይና ግን የነዳጅ ግዥዋን በማሳደግ ላይ ናት፡፡
ቻይና ባሳለፍነው ተመሳሳይ ወራት ከሩሲያ የገዛችው የነዳጅ መጠን ከዘንድሮው ጋር ሲነጻጸር በ60 በመቶ ማደጉን ሩሲያን ቱዴይ (አር.ቲ) ዘግቧል፡፡
አሜሪካ እና ምዕራባውያን ሀገራት ቻይና በሩሲያ ላይ ማዕቀብ እንድትጥል ቢጠይቁም ቤጂንግ ግን ማዕቀብ የሩሲያን እና ዩክሬንን ጦርነት አያስቆምም ስትል ተናግራለች፡፡
አሜሪካ በበኩሏ ከሩሲያ ጋር ንግድ የሚፈጽሙ ሀገራት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማዕቀቡን ካላከበሩም ማዕቀብ እንደሚጣልባቸው አሳስባ ነበር፡፡ የአሜሪካንን ማሳሰቢያ ውድቅ ያደረገችው ቻይና ከሩሲያ ነዳጅ መግዛቷን እንደምትቀጥል ገልጻለች፡፡
ቻይና፤ ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለዓለም "አዲስ ሞዴል" የሚሆን ነው ስትል ገለጸች
ሩሲያ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ለቀድሞዎቹ የሶቪየት ህብረት አባል ሀገራት ነዳጅ ታቀርብ የነበረ ቢሆንም ከጦርነቱ በኋላ ግን የነዳጅ ግዢው በ27 በመቶ ቀንሷል፡፡
ይሁንና ባለፉት አራት ወራት ውስጥ 50 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ነዳጅ ለነዚሁ ሀገራት መሸጧ ተገልጿል፡፡ተብሏል፡፡
ሩሲያ ከመጋቢት መጨረሻ ቀናት ጀምሮ አውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ወዳጅ ላልሆኑ ለሌሎች ሀገራት ነዳጅ በሩብል እንዲሸጥ መወሰኗ ይታወሳል፡፡
የአውሮፓ ህብረት የሩሲያን አዲስ የነዳጅ ግዥ ውሳኔ ውድቅ ያደረገ ቢሆንም የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በበኩሉ ማዕቀቡን ሳይጥሱ የአውሮፓ የነዳጅ ኩባንያዎች ከሩሲያ በሩብል እንዲገዙ ፈቅዷል፡፡
ከ10 በላይ የአውሮፓ ሀገራት ነዳጅ በሩብል ከሩሲያ በመግዛት ላይ ሲሆኑ ፖላንድ እና ቡልጋሪያ ነዳጅ ለመግዛት ሩብል ባለማቅረባቸው ምክንያት ሩሲያ ነዳጅ መሸጥ ማቆሟ አይዘነጋም፡፡