ከቁርዓን መቃጣል የተቆጡ የአረብ ሀገራት የስዊድን አምባሳደርን ለማብራሪያ ከመጥራት ማስጠንቀቂያ እስከ መስጠት ደርሰዋል
ጫና የበረታተበት የስዊድን መንግስት የኢድ አል አድሃ (አፈራ) እለት በሀገሪቱ በተቃዋሚዎች የተፈፀመውን የቅዱስ ቅርዓን የማቃጠል ተግባርን አወገዘ።
የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ባሳለፍነው ሳምንት ሲከበር በስዊድን መዲና ስቶኮልም ተቃዋሚዎች የቅዱስ ቁርአን ማቃጠላቸው በርካታ ሀገራትን አስቆጥቷል።
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኡልፍ ክሪስቴርሰን በወቅቱ በሰጡት መግለጫም፥ ቁርአን የማቃጠሉን ጉዳይ “ተገቢ አይደለም ግን ህጋዊ ነው” በሚል ማለፋቸው አይዘነጋም።
ይህንን ተከትሎም በርካታ ሀገራት ተግባሩን የተቃወሙት ሲሆን በተለይም የአረብ ሀገራት የስዊድን አምባሳደርን ለማብራሪያ ከመጥራት ማስጠንቀቂያ እስከ መስጠት ደርሰዋል።
ጫናው የበረታበት የስዊድን መንግሰትም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በኩል ባወጣው መግለጫ፤ በስቶኮልም መስጊድ አቅራቢያ የተፈጸመውን የቅዱስ ቅርዓን ማቃጠል ተግባር እስላም ጠል በማለት በመፈረጅ ትግባሩን አውግዟል።
ተግባሩን በጽኑ እንደሚያወግዝ ያስተወቀው የስዊድን መንግስት፤ ተግባሩ በምንመ አይነት መንገድ የስዊድን መንግስት አቋምን አይወክልም ብሏል።
የስዊድን መንግስት የውግዘት መግለጫውን ያወጣው መቀመጫውን ሳዑዲ አረቢያ ያደረገው ኢስላሚክ ኮርፖሬሽን (ኦ.አይ.ሲ) ከዚህ በኋላ የቁርዓን ውድመትን ለመከላከል የተጠናከረ እርምጅ እንዲወሰድ ጥሪ ማቁረቡን ተከትሎ ነው።
57 አባላት ያሉት የኢስላሚክ ኮርፖሬሽን (ኦ.አይ.ሲ) በስድን የተፈጸመውን የቁርዓን ማቃጠል ተግባር ተከትሎ በሳዑዲ አረቢያ ጄዳህ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ ከሰሞኑ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር።
በስብሰባውም አባል ሀገራቱ ከዚህ በኋላ በቅዱስ ቁርዓን እና ሌሎችም ቁዱሳን ተቋማትና መግለጌዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል የተማከለ እና በትብብር እርመጅ ሊወሰድ እንደሚገባ ከስምምነት መድረሱ ተነግሯል።